በአርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒከስ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤የመኪና ጎማዎችና ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በአርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒከስ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤የመኪና ጎማዎችና ሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የተወዳዳሪዎች መመሪያ
1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብርከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ እና በፌደራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 400.00 ( አራት መቶ ) በጮሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000063129848 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ጉዳይ ቢሮ ቁጥር WM 08 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ከግብር : ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትከክል ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፣ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ መ/ቤት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ጨረታ ላይ : ባይገኙም የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
6. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይከዋለ የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይየስራ ሰዓት ይሆናል፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች ለሚገዛው ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 ( ሰላሳ ሺህ)፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በከፍያ ማዘዣ (CP.O.) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
8. ተጫራቾች ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ያዘጋጀውን የእቃ ናሙና በማየት ዋጋ በመሙላት መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
9. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
10. አሸናፊው ተጫራች ፈርኒቸሮችን ገጣጥሞና ኤሌክትሮኒክስ መለያ ቁጥሩን አስመዝግቦ በሚመደበው ባለሙያ የእቃዎች ጥራትና ብቃት ተረጋግጦ ገቢ ከተደረገ በኋላ ከፍያ የሚጸም ይሆናል፡፡
11.ጽ/ቤቱ የእቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ 20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡
12. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 0912809688/ 0915839978፣0915804892 ይጠይቁ፡፡
በአርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ኦሮሚያ ክልል
