የፅህፈት መሳሪያዎች፣ አላቂ እና ቋሚ የቢሮ ውስጥ ማገልገያ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማሽኖች እና የICT እቃዎች ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ባሌ ዞን ዳዌታችን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ 2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለማገኙ መንግስት መ/ቤቶች የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ አላቂ እና ቋሚ የቢሮ ውስጥ ማገልገያ ዕቃዎች የደንብ ልብስ ፣ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ማሽኖች እና የICT እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በዚህ መሠረት ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ሕጋዊ ድርጅት መወዳድር ይችላል ፡ ፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒና ኦርጅናል ዶክሜንት ማቅረብ የሚችል
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸው ማረጋገጫ ሰርትፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የVAT ተመዝጋቢ ወይም የፐOT ተጠቃሚ ሆኖ ናቸው የሚያስረዳ መተማመኛ ማቅረብ የሚችሉ
- ማንኛውም ተጫራች በተወዳደሩበት እቃ በጨረታው ዝርዝር ሰነድ ላይ ሞዴልና ብራንድ (model and Brand) ካልሞሉበት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው በሰም በታሸ ኢንቨሎፕ አድርገው በመፈረም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 2% (ሁለት ፐርሰንት) በባንክ በተሰመሰከረለት ኦርጅናል CPO በዶኩሜንት ውስጥ አስገብቶ በማሸግ ወይም 30,000(ሰላሳ ሺህ) ብር በእጅ በካሽ ማስረከብ አለባቸው
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታው መሳተፍ ይቻላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋ አስር ፐርስንት (10%) በጥሬገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት (5) የስራ ቀናት ውስጥ በአካል በመገኘት የውል ስምምነት መፈፀም ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለተሸናፊ ተጫራቾች ጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙች CPO ወዲያውኑ የሚመለስ ላቸው ሲሆን የጨረታ አሽናፊዎች ግን የውል ማስከበሪያ እንዳስያዙ ላልተወሰ ጊዜ ይቆያል
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት 16ኛው ቀን አራት ሰዓት ተኩል (4፡30) ተዘግቶ አምስት ሰዓት (5፡00) ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወከዮቻቸው በተንኙበት በዳዌቃችን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡ ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪል ያልተገዩበት ሰነድ በጭራሽ አይከፈትም፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እሁድ ወይም በበዓለትን ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ እና ሰዓት የመዝጊያ አእና መክፈታ ቀን ይሆናል፡፡
- ተወዳዳሪዎች በህግ የተደነገጉ እና በጋዜጣው ላይ የወጡትን ማንኛውን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
- ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት ማንኛውም መረጃ ላይ ለፖስታ ውጭ ሆነ ውስጥ ፊርማ እና ህጋዊ ማህተም ሊኖረው ይገባል ከሌለው ግን ተቀባይነት የለውም፡፡
- በማይከሮ የተደረጁ ማህበራት (IMX) ይበረታታሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች የማጓጓዢያ መጪዎችን በሙሉ እስከ ዳዌቃችን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ድረስ መሸፈን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ለተሰበሩ ዕቃዎች ወይም አገልግሎት መስጠት ለማይችሉ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ዋጋ አይከፍልም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመዘረዝ ሙሉ መብት አለው ፡፡
- ተወዳደሪዎች በሚያቀርቡት ማንኛውም ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለበት ተቀባይነት የለውም
- የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ከዳዌቃቸን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር ብቻ በመከለል መግዛት ይቻላል፡፡
➢ ለበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-11-14-62-40 ወይም በ 09-22-32-83-01 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምሥራቅ ባሌ ዞን ዳዌቃችን ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of office supplies, uniforms, technical training machines, and ICT equipment for government offices in Dawe Kachen District, Oromia. Open tender for legal entities with valid licenses, tax clearance, registration, and VAT/TOT status. Bidders must specify model and brand.
