የቢሮ ዕቃዎች፣ መሳሪያዎች፣ አገልግሎቶች እና ሌሎች ዕቃዎች ግዥ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ወ-01-01-/2019
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት ሎት1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት2. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት3 ማሽነሪ ቋሚ ዕቃዎች ሎት4 የደንብ ልብስ ሎት 5 የፅዳት ዕቃዎች ሎት6 የህትመት አገልግሎት ሎት 7 መስተንግዶ አገልግሎት ሎት 8 የመኪና ኪራይ አገልግሎት ሎት 9 የጉልበት አገልግሎት ሎት 10 የቢሮ ቁሳቁስ ጥገና ሎት 11 የኮምፒዩተር ጥገና ሎት12 የዲኮር አገልግሎት ሎት13 የቢሮ ቁሳቁስ ቋሚ ዕቃ ሎት14 የመኪና ዕቃዎች ሎት15 የአትክልት ዘር ሎት16 የእንስሳት ህክምና መዳኃኒቶች እና ቁሳቁስ ከላይ በዝርዝር የተገለጹትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
v በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
v ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
v ተጫራቾች የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ሰነድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መያያዝ አለባቸው።
v ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መረጃቸው መገኘት የሚችል።
v ተጫራቾች ለመጫረት የሚፈልጉትን የጨረታ አይነት የዕቃዎች ናሙና በየሎቱ በማድረግ የሚያስፈልጉ ናሙናዎችን በሙሉ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ባሉት ቀናት ውስጥ ቦታው ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
v ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሎት1 ብር 6,000/ስድስት ሺህ ብር/ ሎት 2 ብር 5,000/አምስት ሺህ ብር ሎት3 ብር 6,000/ስድስት ሺህ ብር/ ሎት4 ብር 6,000 ስድስት ሺህ ብር/ ሎት5 ብር 3,000/ሶስት ሺህ ብር/ ሎት 6 ብር 4,000/አራት ሺህ ብር/ ሎት 7 ብር 5,000/አምስት ሺህ ብር / ሎት 8 ብር 5,000/አምስት ሺህ ብር/ ሎት 9 ብር 3,000/ሶስት ሺህ ብር/ ሎት 10 ብር 6,000/ ስድስት ሺህ ብር/ ሎት 11 ብር 6,000/ስድስት ሺህ ብር/ ሎት 12 ብር 5,000/አምስት ሺህ ብር/ ሎት 13 ብር 6,000/ስድስት ሺህ ብር/ ሎት 14 ብር 6,000/ስድስት ሺህ ብር/ ሎት 15 ብር 3,000/ሶስት ሺህ ብር/ ሎት16 ብር 3,000 / ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ በየሎቱ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
v ተጫራቾች ከላይ ከተዘረዘሩት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
v አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
v ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ አቅራቢዎች የጨረታውን ሰነድ አየር ጤና ታክሲ ተራ አዲሱ አስፓልት ቴሌ ግቢ በሚወስደው መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ የሚገኘው ወረዳ 01 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 009 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10ኛው ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በየሎቱ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
v ተጫራቾች በ11ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የማይሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
v ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በፖስታ ላይ በመፃፍ በማሽግ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውሰጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ማስገባት አለባቸው።
v ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ይከፈታል።
v ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ካሌንደር የሚዘጋው ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተጠቀሰው ቢሮ ይከፈታል።
v ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚገዙበት ወቅት ሰነድ የሚሸጠው በየሎቱ ተለይቶ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
v አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ7(ሰባት) የስራ ቀናት በኋላ የውል ማስከበርያ ይዞ በመቅረብ ውል መዋዋል አለበት ካልቀረበ የጨረታ ማስከበርያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
v ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
v ጨረታው የሚሞላው ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ከቫት ውጭ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
v ተጫራቾች የጨረታ መመሪያውን ከሰነድ ጋር በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
v ለመኪና ኪራይ አገልግሎት፤ ለጉልበት ስራ አገልግሎት፤ የንግድ ፈቃድ፤ የግብር መለያ ቁጥር፤ የንግድ ምዝገባ ብቻ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
v ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፡-
በስልክ ቁጥር 011-3-48 66-08 /011–3-69-42-06 መጠየቅ ይችላሉ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት
