Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል
  • Address ሞጆ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0221162194
  • Website
  • Deadline23 Aug 2026, 4:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price
  • opening dateየጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ቀን እና ሰዓት ይሆናል
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services

የተለያዩ የጽዳት እና የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር- ESLSE/P&T/REQ/2025/37354

በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል ለ2019 በጀት አመት የሚውሉ የተለያዩ የጽዳት እና የጽህፈት መሳሪያዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

·        ሎት- አንድ፡ የጽዳት እቃዎች ጨረታ ግዥ

·        ሎት- ሁለት፡ የጽህፈት መሳሪያዎች ጨረታ ግዥ

በዚህም መሰረት፦

1.      በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት የምስክር ወረቀት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2.    በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ድህረ ገፅ (web site) ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን የሚያሳይ (supplier list) የምስክር ወረቀት፤

3.    የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ ስልጣን ካለው አካል የተሰጠ ማስረጃ (Volid tax clearance)።

4.    ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ የሚመልሰው በድርጅቱ ድህረ-ገጽ (WWW.ESLSE.COM (https://www.eslse.com/)) ላይ በERP SYSTEM በዋና መ/ቤት ምዝገባ ካካሄዱ በኋላ ብቻ (ከዚህ ቀደም ያልተመዘገቡ ከሆነ) በሚሰጣቸው መለያ ቁጥር መሰረት የሚሞሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

5.    የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ቀን እና ሰዓት ይሆናል።

6.    የጨረታ ማስያዣ ሲ.ፒ.ኦ 50,000 ብር (ከንግድ ባንክ፤ ከህብረት ባንክ እና ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ብቻ) ለእያንዳንዱ ሎቶች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በማዕከሉ የሚገባ ይሆናል።

7.    ማንኛውም ተጫራች ለሚወዳደርባቸው እቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፣

8.    ቅ/ ጽ/ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ በስልክ ቁጥር 022 116 2194 

ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል

✨ messages.ai_summary
Procurement of various cleaning and office supplies by Ethiopian Maritime Transport and Logistics Mojo Logistics Center via open national tender, split into two lots: cleaning items and office supplies. Bidders need valid business licenses, tax clearance, VAT certificate, and supplier registration.
Save Tender