በቡኖ በደሌ ዞን የገቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም የበጀት ዓመት በወረዳችን ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የሚዉሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
በቡኖ በደሌ ዞን የገቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም የበጀት ዓመት በወረዳችን ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የሚዉሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1.የአላቂ ዕቃዎች እና እስቴሽነሪዎች 2.የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 3. የሰራተኞች የደንብ ልብስ 4. ሞተር ሳይክሎች 5.የፈርኒቸር ዕቃዎች 6.የመኪና እና ሞተር ሳይክል ጎማ 7.የግንባታ ዕቃዎች ማቅረብ የሚችል።
በጨረታዉ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. ተወዳዳሪዎች በአካባቢያቸዉ ከሚገኘዉ የገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት የ2018 የዘመኑን ግብር መክፈላቸዉን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
3. በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ ተመዝጋቢ መሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
4. ማንኛውም ተወዳዳሪ ለእያንዳንዱ ሰነድ 100,000 (አንድ መቶ ሺ) በአቅርቢያችን ከሚገኝ ባንክ በመ/ቤታች የባንክ አካውንት የገባበት SLEP ከጨረታዉ ሰነድ ግዥ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል
5. አሸናፊ ተጫራቾች የዉል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋን 10% በባንክ በተመሰከረ SLEP ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. አሸናፊ ተጫራቾች ለእያንዳዱ ሰነድ ያስያዙትን SLEP ያሸነፉበት የዕቃ ሙሉ በሙሉ ካላቀረቡ SLEPቸው የማይመለስ ይሆናል።
7. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ 90 (እስከ ህዳር 30/2019)ቀናት ይሆናል።
8. ዕቃውን ማስረከሚያ ቦታ ገቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ሆኖ ጠቅላላ ወጪ የሻጩ ግዴታዎች ናቸው።
9. አሸናፊ ደርጅት ጥራት የሌላቸዉና ያልተጠየቁ እቃዎችን ካቀረቡ ተቀባይነት የለዉም።
10. በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋን ማቅረብ አይቻልም።
11. የዕቃው ብዛት 20% ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል።
12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸዉን እቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
13. ተወዳዳሪው የእቃውን ዋጋ ሲሞላ ቫት ጨምሮ መሙላት አለበት። ካልሞላ ግን ቫት እንደተጨመረ ተደርጎ ይወሰዳል።
14. በደንብ ልብስ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሰነዱን ሲያስገቡ የእቃዎችን ናሙና ማቅረብ አለባቸዉ።
15. ፈርኒቸር እቃዎች ተወዳድረዉ ያሸነፉ ተጫራቾች እቃዉን ገጣጥመዉ ማስረከብ አለባቸዉ።
16. አሸናፊ ድርጅት በእያንዳንዱ ሴክተር መ/ቤት ደረሰኝ መስጠት አለበት።
17. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲያቀርቡ ቴክኒኩን ኦሪጅናል እና ኮፕዉን በተለያዩ ፖስታ እንድሁም የፋይናንስ ዋጋ ኦሪጅና እና ኮፒዉን በተለያዩ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ።
18. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ለተከታታይ ለ15 የስራ ቀናት 12/12/2018 እስከ 3/13/2018 በአየር ላይ የ ሚቆይ ሲሆን ፤ የጨረታዉን ሰነድ ከገቺ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 7 የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመግዛት ዋጋቻዉን ሰነዳቸዉ በተዘጋጀ ሳጥን ዉስጥ በወረዳዉ ገ/ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት ይችላሉ።
19. ጨረታው በ15ኛ የስራ ቀናት 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታዉን አያስተጋጉልም።
20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 047 340 0475, 09 13 51 86 38
በቡኖ በደሌ ዞን የገቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
