Tender Detail

Tender Details


በቂርቆስ ክ/ከ የእውቀት ፋና ቅድመ አንደኛ፡ እንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ 2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማስጠገን ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በቂርቆስ ክ/ከ የእውቀት ፋና ቅድመ አንደኛ፡ እንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ 2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማስጠገን ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ
  • ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 3. የህትመት ውጤቶች
  • ሎት 4. አላቂ የህክምና እቃዎች
  • ሎት 5. አላቂ የትምህርት እቃዎች
  • ሎት 6. የተለያዩ መሳሪያዎችና መጽሀፍቶች
  • ሎት 7. ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያዎች መግዣ (ቋሚ እቃ)
  • ሎት 8. ለህንጻ ሰቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ መግዣ
  • ሎት 9. ለፕላንትና ለማሽነሪ መሳሪያዎች ጥገና (ኤሌክትሮኒክስ)
  • ሎት 10. ሌሎች አላቂ የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 11. የበር ስራ የጥበቃ ማማ፤ ቁሳቁስ ጥገና

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባችሁ ቅድመ ሁኔታዎች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የንግድ ምዝገባ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
  4. የቫት ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  6. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች ከተደራጁበት ከፍለ ከተማ ወይም ወረዳ በመስሪያ ቤቱ ስም የተፃፈ ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
ሎትየእቃው ዓይነትየጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የብር መጠን
1የደንብ ልብስ5,000.00
2አላቂ የቢሮ እቃዎች5,000.00
3የህትመት ውጤቶች2,000.00
4አላቂ የህክምና እቃዎች3,000.00
5አላቂ የትምህርት እቃዎች5,000.00
6የተለያዩ መሳሪያዎችና መጽሀፍቶች3,000.00
7ለፕላንት ለማሽነሪና ለመሳሪያ መግዣ (ቋሚ እቃ)3,000.00
8ለህንጻ ሰቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ መግዣ5,000.00
9ለፕላንትና ለማሽነሪ መሳሪያዎች ጥገና (ኤሌክትሮኒክስ)4,000.00
10አላቂ የጽዳት እቃዎች5,000.00
11የበር ስራ) የጥበቃ ማማ፣ ቁሳቁስ ጥገና5,000.00
  1. ለጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) የማይመለስ በመከፈል ይህ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ የእውቀት ፋና ቅ/አ/አ/መካ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 04 በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃ ናሙና ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል ብሎ በመለየት በፖስታ አሽገው ሲመጡ (CPO)ውን እና ተያያዥ መረጃዎች ደግሞ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል ባለበት ፖስታ ውስጥ ማስገባትና በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በዝርዝር ሰነድ ላይ ባለው ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀናት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን በቢሮ ቁጥር 04 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው በወጣበት 11ኛው የስራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ጠቅላላ ዋጋ 10 % በእውቀት ፋና ቅ/መካ/ደ/ት/ቤት ስም በባንክ በተመሰከረ (CPO) ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
  7. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ 0114162240/0114161169 APK (አድራሻ፡- ከጠመንጃያዥ ባንክ በስተጀርባ ከቀድሞው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በአሁኑ ፋና ሬድዮ ጣቢያ በግምት 500 ሜ ገባ ብሎ ወይም ከቂርቆስ ቤተከርስቲያን በአዲሱ አስፓልት ከአድባር ሆቴል በግምት 200 ሜትር ወረድ ብሎ ይገኛል፡፡

በቂርቆስ ክ/ከተማ የእውቀት ፋና ቅ/ስ/ስ/መካ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for purchasing and repairing various items for a school in Kirkos sub-city, including uniforms, office supplies, printing, medical and educational materials, equipment, books, construction supplies, electronics repair, cleaning items, and maintenance work. Bidders must have valid licenses, tax clearance, TIN, VAT registration, and supplier registration.
Save Tender