በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፤ የጽዳት እቃዎችን፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፤ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሳሪያ፤ የጽዳት እቃዎችን፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፤ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች:-
- በዚህ ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ያለው የ2018/2019 የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በአስር ቀን ውስጥ ያሸነፋቸውን እቃዎች ገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የያዘ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን በስራ ሰዓት እስከ 6፡30 ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1055210501213 በመክፈል የባንክ ስሊፕ በማምጣትና ከገቢዎች በማወራረድ ከገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን እቃ የሚሸጡበትን ዋጋ የያዘ ዝርዝር የዋጋ ሰነድ በፖስታ በማሸግ ጋዜጣ ከወጣት በ16ኛው ቀን እስከ 8:00 ሰዓት ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ ወይም ሲፒኦ በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ያስገባሉ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
- በሌላ ሰው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች ለሙያቸው ማረጋገጫ የስራ ልምድ እና የምስጋና ደብዳቤ ቢያቀርቡ ይመረጣል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0920762750 /0910285005 / 0922831458 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የገርበ ጉራቻ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Tender for procurement of office supplies, cleaning materials, office furniture, electronics, vehicle tires, and staff uniforms for sector offices under Gerba Guracha Town Finance Office, Oromia. Bidders need valid trade license, tax clearance, and registration with Ministry of Finance.
