Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአርሲ ዞን የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address አርሲ ዴራ ከአዳማ በአሰሳ መስመር 25 ኪ.ሜ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-12-26-33-11
  • Website
  • Deadline02 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከረፋዱ 04:30
  • Categories Furniture And Furnishing , Electrical And Electromechanical , Office Supplies And Services

የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ ውስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019

የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የቢሮ ውስጥ ልዩ ልዩ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:-

  1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer Registration number) ያላቸው እና በፌዴራል በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ለጽሕፈት መሣሪያዎች ለጽዳት እቃዎች ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በጽሕፈት ቤቱ ስም በሲንቁ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1071392621217 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽሕፈት ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 04:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት የጽሕፈት ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡
  4. እለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሰው መሰረት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. አሸናፊው ተጫራች ያለ ምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ አስፈላጊ የሆነ የዕቃ አቅም ያለውና ዕቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ዴራ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች እስክሪብቶዎች፣ የፕሪንተር ቀለሞች እና ደንብ ልብስ ሌላ የሚወዳደርለት/የሚወዳደሩበት እቃ ናሙና (ሳምፕል) ማቅረብ አለበት፡፡
  8. ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ላሸነፈበት ዕቃ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መግባት ይጠበቅበታል፤ ለውል ማስከበሪያም ያሸነፈበት ከእቃ ዋጋ 10% በካሽ ወይም በ(CPO) ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡

ዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት አርሲ ዴራ ከ አዳማ በአሰላ መስመር 25 ኪሜ

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (091226331) (0910770359) (0982517409) ይጠይቁ፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአርሲ ዞን የዴራ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of office furniture, electronics, stationery, cleaning supplies, staff uniforms, and vehicle tires for sector offices in Dera Town. Bidders must hold valid trade licenses, VAT registration, tax ID, and supplier certificates. Samples required for certain items.
Save Tender