በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ከ/ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች ያሉትን እቃዎች እነዚህም፦ ሎት1 የስቴሽነሪ እቃ፣ ሎት2 የስፖርት እቃ፣ ሎት3 ቋሚ እቃ፣ ሎት4 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት5 የደንብ ልብስ፣ ሎት6 የኤሌከትሪከ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ከ/ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች ያሉትን እቃዎች እነዚህም፦ ሎት1 የስቴሽነሪ እቃ፣ ሎት2 የስፖርት እቃ፣ ሎት3 ቋሚ እቃ፣ ሎት4 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት5 የደንብ ልብስ፣ ሎት6 የኤሌከትሪከ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሆን አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የምዘገባና ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O ማቅረብ አለባችሁ፡፡
| የሎት ቁጥር | የሎት ዝርዝር | የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
| ሎት1 | የስቴሽነሪ እቃ | ብር 1000 |
| ሎት2 | የስፖርት እቃ | ብር 1000 |
| ሎት 3 | ቋሚ እቃ | ብር 1500 |
| ሎት4 | የፅዳት እቃ | ብር 1500 |
| ሎት5 | የደንብ ልብሰ | ብር 1500 |
| ሎት6 | የኤሌከትሮኒክስ እቃ | ብር 2000 |
- የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን 14/12/2018 ዓ.ም ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100.00/መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ፋይናንስ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚጠናቀቅበት ቀን 29/12/2018 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የግዥ ቢሮ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ማቅረብ ለማይቻልባቸው ፎቶ ወይም ብሮሸር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፋችሁበትን እቃ በራሳችሁ ትራንስፖርት ንብረት ከፍል ድረስ ማስገባት አለባችሁ፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- 22 ዘሪሁን ህንፃ 100ሜትር ገባ ብሎ በተለምዶ ሜከሊላንድ ጎዳና
ለበስጠ መረጃ፡- 0116663976 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ክፍስ ከተማ አስተዳደር የዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for supplying stationery, sports equipment, fixed assets, cleaning supplies, uniforms, and electronics in six lots to Dr. Hadis Alemayehu 2nd Cycle School, Bole Sub-city. Bidders need valid licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
