Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት 1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 0913151293
  • Website
  • Deadline31 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • opening dateበአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Categories Education And Training , Health Care, Medical Industry , Office Supplies And Services

አበባ ማረሚያ ቤት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡-0001/2019

አበባ ማረሚያ ቤት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች፡-

  1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ሁ/ደ/ት/ቤት ስም በባንክ ሲፒኦ (CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፍበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት፡፡
  6. ይህ ጨረታ ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ብቻ ነው፡፡
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአዲስ አበባ ማረሚያ የሁ/ደ/ት/ቤት (በቃሊቲ ማረሚያ ቤት) በፋይናንስ ቢሮ ቁ.3 ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከትምህርት ቤቱ ግዢ እና ንብረት አስተዳደር የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በዝዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻው ቦታ ላይ ስም ፣ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎጥ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-1፡30 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ ከታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
1 ሎት1 6211 ደንብ ልብስ ብር 30,000.00
2 ሎት2- 6212 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ብር15,000.00
3 ሎት3- 6214 አላቂ የህክምና ዕቃዎች ብር 6,000.00
4 ሎት4- 6215 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ብር 30,000.00
5 ሎት5- 6218 የዕዳት ዕቃዎች ብር 40,000.00
6 ሎት6- 6219 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 10,000.00
7 ሎት7- 6313 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ብር 40,000.00
  1. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርቦታል፡፡
  3. ጨረታውን ለማባዛት የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበሪያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው፡፡
  4. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዝ የተደራጁ አምራች ድርጅቶች የዋስትና ደብዳቤ ካደራጃቸው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ አምራች ካልሆኑ ደግሞ አምራች ከሆነው የሀገርውስጥ ድርጅት ትስስር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ይቆይና በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ይዘጋና ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊቲ ከ/ከ ክራውን ሆቴል ፊት ለፊት ፌዴራል ማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር፦ 0988364945/0988316045

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ሁስተኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of various goods for Addis Ababa prison secondary school's 2019 budget year. Bidders must be registered government suppliers, VAT-registered, hold valid trade licenses, and have paid current taxes.
Save Tender