በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የሕንፃ መሣሪያ ፈርኒቸሮችን፣ የቤትና ቢሮ ቋሚ ዕቃዎችን፣ የፋብሪካ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን፣ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የሕንፃ መሣሪያ ፈርኒቸሮችን፣ የቤትና ቢሮ ቋሚ ዕቃዎችን፣ የፋብሪካ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላትና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ መረጃ ማቅረብ የምችሉ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ያላት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
- ቫት በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ካልተለጠፈ እንደተገለጸ ተደርጎ ይወሰዳል
- ተጫራቾች የቴክኒክና ፋይናንሻል ሰነድ አንድ (1) አርጅናልና አንድ (1) ኮፒ ጋር ማቅረብ አለባቸው፣ በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ አድራሻ ተጽፎ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ወጪ ወደ ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ /Bid bond/ 20,000/ ሀያ ሺህ ብር /በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆየው በጨረታ ያሸነፉትን ዕቃ ሙሉ በሙሉ እስኪያቀርቡ ድረስ ነው፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 25 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር በጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመከፈል መግዛት የሚችል /የምትችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 በሥራ ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ተኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ በሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የአሸናፊ ድርጅት ውል ለመግባት ሲመጣ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበት ዋጋ 10% CPO ማቅረብ የሚችል /የምትችል መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸው ዋጋ ከውል ጊዜ ጀምሮ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት የጸና ይሆናል።
ማሳሰቢያ:-
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በአንዱ ዋጋ ላይ ዋጋ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም፡፡
- የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0944708656 / 0916345359
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን የጨንቻ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of office supplies, cleaning materials, electronics, furniture, and other goods for sector offices in Chencha Zuria district. Bidders need valid trade license, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
