Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀሳባ ዞን ቁሲቶ አጠቃላይ ሆስፒታል
  • Address Central Ethiopia Regional state, Phone: 0465560281/0926182111/0941985 165
  • Website
  • Deadline05 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/
  • opening dateበ16ኛው የስራ ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Office And Home Furniture

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት በጨረታ መለያ ቁጥር ሀ/አጠ/ሆ 01/2018 ለሆስፒታሉ ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሳሪያ፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የፅዳት እቃዎችን፣ የኤሌክትሪክ እቃዎችን እና ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች እና ነጋዴዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ መለያ ቁጥር ሀ/አጠ/ሆ 01/2018

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት በጨረታ መለያ ቁጥር ሀ/አጠ/ሆ 01/2018 ለሆስፒታሉ ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ የፅህፈት መሳሪያ፣ የቢሮ ፈርኒቸር፣ የፅዳት እቃዎችን፣ የኤሌክትሪክ እቃዎችን እና ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች እና ነጋዴዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው መሳታፍ የሚፈልጉ ተጫረቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1.      ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ኦርጅናል እና ኮፒ፣ የመንግሥት አገልግሎት ግዥ በአቅራቢነት ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኦሪጅናልና ኮፒ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ክፍያ ምስክር ወረቀት/TIN number/ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.    እያንዳንዳቸው ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000/አስር ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ /RV/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

3.    ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማኖር ዋናውን ሰነድ በአግባቡ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በግልፅ ኤንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታክስን /VAT/ የሚያካትት መሆን አለበት። ካልሆነ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።

4.    የጨረታ ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በመደበኛ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 57 በአካል በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በስራ ሰዓት ቀርበው መወሰድ ይችላሉ።

5.    የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ቀን ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሳጥኑ ይከፈታል። ነገር ግን 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

6.    አሸናፊ የሆነ አቅራቢ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ እንዲሁም የትራንስፖርት በራሱ ወጪ የሚያቀርብ ይሆናል።

7.    መ/ቤቱ የተሻለ አማረጭ ከገኛ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 556 0281 / 09 41 98 51 65 / 09 28 18 21 11 ላይ መደወል ይቻላል።

አድራሻ፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊንቶ አጠቃላይ ሆስፒታል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሀላባ ዞን ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Open tender for office supplies, furniture, cleaning items, electrical goods, and uniforms for Kulito General Hospital. Bidders must hold a valid renewed trade license, business registration, and TIN. Delivery and transport costs are the winner's responsibility.
Save Tender