Tender Detail

Tender Details

  • Company Moha Soft Drinks Industry Co., Ltd (ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር)
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ አዲስ በተገነባው ህንጻ 3ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251116614655
  • Websitehttps://mohasoftdrinks.com/
  • Deadline07 Sep 2026, 2:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • opening date9፡00 ላይ
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Transportation Service And Cargo

የፅህፈት መሳሪያዎች የፅዳት እቃዎች ሽሪንክ ፊልም፤የተለያዩ ፕሪፎርሞች እና የትራንስፖርት አገልግሎት የጨረታ ግዥ ማስታወቂያ


የፅህፈት መሳሪያዎች የፅዳት እቃዎች ሽሪንክ ፊልም፤የተለያዩ ፕሪፎርሞች እና የትራንስፖርት አገልግሎት የጨረታ ግዥ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር - Service 0004/2018

ሞሃ የስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የፅህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎች ሽሪንክ ፊልም፤የተለያዩ ፕሪፎርሞች እና የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የተጠቀሱትን አገልግሎት ማቅረብ የምትችሉ ተጫራች ድርጅቶች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥርግቢ አዲስ በተገነባው ህንጻ ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 003 በመውሰድ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፤VAT እና TIN ያላቸውና የግብር ግዴታቸውን የተወጡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን አገልግሎት የምትሰጡበትን ዋጋችሁን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎች ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም እና ፕሪፎርም እና ሽሪንክ ፊልም ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ከላይ በተገለፀው መ/ቤት አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ከተጠቀሰው ሰዓት በኋላ ዋጋ ለማቅረብ የሚመጣ አቅራቢ ተቀባነት አይኖረውም፡፡
  4. የፅህፈት እና የፅዳት እቃዎች ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 9፡00 ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በዋናው መ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
  5. የትራንስፖርት አገልግሎት ጳጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 9፡00 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በዋናው መ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
  6. ፕሪፎርም እና ሽሪንክ ፊልም ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 9፡00 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በዋናው መ/ቤት መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፊት ይከፈታል፡፡
  7. በጨረታው የሚሳተፍ ድርጅት 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፦ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸገር ዱቄትና ዳቦ ፋብሪካ ቅጥርግቢ አዲስ በተገነባው ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግና የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።

ሞሃ የስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማ

✨ messages.ai_summary
Moha Soft Drinks Industry seeks bids for office supplies, cleaning materials, shrink film, various preforms, and transport services. Bidders must hold a valid business license, VAT, TIN, and tax clearance. A 50,000 birr CPO bid security is required.
Save Tender