የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2019 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የተለያዩ ሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2019 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የተለያዩ ሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. የጽዳት ዕቃዎችን እና
- ሎት 2. ስቴሽነሪ
ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፤ ስለዕቃዎቹ የሚገልጽ ሰነድ (ዶክመንት) በወራቤ ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች ተፈላጊ ዕቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዋጋ 20000 ብር /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ CPO/ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-6፡30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡30 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ስራ አስፈጻሚ ክፍል ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ08፡00 ተዘግቶ በ15ኛ ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመከፈቻውም ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ለሚያቀርቡት ዕቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ግዴታ ነው።
- ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463299263 ደውሱ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
✨ messages.ai_summary
Worabe Comprehensive Specialized Hospital seeks bids for cleaning supplies (Lot 1) and stationery (Lot 2). Bidders need valid licenses, VAT registration, TIN, supplier registration, and must submit samples.
