በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ከ/ከተማ በወረዳ 06 በምስራቅ በር ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ ጨረታ መስያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ከ/ከተማ በወረዳ 06 በምስራቅ በር ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት አላቂ የቢሮ እታ ፡ ሎት2 አላቂ የትምህርት እታ፡ ሎት3 የደንብ ልብስ ፡ ሎት4 ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት5 የዕዳት ዕቃ (ሎት6 ቋሚ ዕታ ( ሎት7 የህከምና ዕቃ (ሎት8 የድንብ ልብስ ስፌት (ሎት9 ህትመት፤ ሎት10 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች (ሎት11 የማሽነሪ ጥገና& ሎት12 የትራንስፖርት አገልግሎት እና ሎት13 የጭነት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
1. ተጫራች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘነበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው:
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስከር ወረቀት እና ከሪላንስ እስከተፈቀደለት ቀን ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፤
5. ተጨራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በደብዳቤ ከሆነ ከአደራጃቸው ተቋም ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው:: በCPO ከሆነ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማቅረብ አለባቸው ::
|
የሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን |
|
ሎት1 |
አላቂ የቢሮ እቃ |
20,000 |
|
ሎት2 |
አላቂ የትምህርት እቃ |
9,000 |
|
ሎት3 |
የደንብ ልብስ |
17,000 |
|
ሎት4 |
ቋሚ ኤሌክትሮኒከስ |
16,280 |
|
ሎት5 |
የፅዳት እቃ |
17,000 |
|
ሎት6 |
ቋሚ እቃ |
5,000 |
|
ሎት7 |
የህክምና እቃ |
500 |
|
ሎት8 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
8,500 |
|
ሎት9 |
ህትመት |
2,000 |
|
ሎት11 |
የማሽነሪ ጥገና |
2,000 |
|
ሎት12 |
የትራንስፖርት አገልግሎት |
3,500 |
|
ሎት13 |
የጭነት አገልግሎት |
6,500 |
6. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100(እንድ መቶ ብር) በመከፈል እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከአደራጃችሁ ተቋም ደብዳቤ በማምጣት የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 5 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቶች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
8. ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በማግስቱ 4፡30 በት/ቤቱ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው::
10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ም/በር ቁ.2/ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
12. ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20%የመቀነስም ሆነ20% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. በሚወዳደሩበት የሎት መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ድምር መጠን ልክ መሆን አለበት፡፡
14. ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
15. አማራጭ ጨረታ አይፈቅድም ግዢ ፈፃሚው
16. የታወቁ ጉዳቶች የካሳ ከፍያ የገንዘብ መጠን በቀን 0.1% ይሆናል
17. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ መገናኛ ቦሴ ክ/ከተማ ጀርባ በሚገኘው ምስራቅበር ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ሲሆን ስልክ
ቁጥር 0116676650
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 06 ምስራቅ በር ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
