Tender Detail

Tender Details

  • Company የጅማ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል /ጅማ/
  • Address Oromia Ethiopia, Phone: 0471112424 ወይም በሞባይል 0917054361
  • Website
  • Deadline10 Sep 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 400 /አራት መቶ ብር/
  • opening dateበ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Hand Tools And Workshop Equipment , Office Supplies And Services

የጅማ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዘመን የሚያስፈልጉ የጽዳት እቃ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የወርክሾፕ መሣሪያዎች፣ ብረታብረትና ሌሎች የምርምር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጅማ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ለ2019 ዓ.ም የበጀት ዘመን የሚያስፈልጉ የጽዳት እቃ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የወርክሾፕ መሣሪያዎች፣ ብረታብረትና ሌሎች የምርምር ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ዝርዝር ሁኔታዎች

ተጫራቾች ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለዕቃዎቹ የሚገልጽ ሰነድ /ዶክመንት/ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ጅማ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ሕንፃ ቁጥር 3 ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

የተጫራቾች መስፈርቶች፡-

  1. ተጫራቾች ተፈላጊ እቃዎችን ማቅረብ የሚያስችላቸው የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለዚህም ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የቫት /የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ተመዝጋቢና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  3. የዚህ ጨረታ ተካፋዮች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸውና ኦሪጅናልና ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ CPO /ሲፒኦ/ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 2:30-6:30 ከሰዓት ከ7:30-11:30 ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  6. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል። የመከፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በሕዝባዊ በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  7. ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦

የስልክ ቁጥሮች 0471112424 ወይም በሞባይል 0917054361 መደወል ይቻላል፡፡

የጅማ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል /ጅማ/

✨ messages.ai_summary
Jimma Agricultural Engineering Research Center seeks bids to procure cleaning supplies, office equipment, workshop tools, metals, and other research items for the 2019 budget year. Bidders must hold a valid trade license, VAT registration, and supplier registration certificate.
Save Tender