በሸገር ከተማ ሱሉልታ ከ/ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለሚገኙ ሴክተሮች የጽህፈት መሣሪያዎች፡- አላቂ ፣የጽዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር መመሪያ Bidders instruction
የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ ሱሉልታ ከ/ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለሚገኙ ሴክተሮች የጽህፈት መሣሪያዎች፡- አላቂ ፣የጽዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር መመሪያ Bidders instruction
ሀ. የተወዳዳሪዎች መመሪያ
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆኖ ሀ. የዘመኑን ግብር በመከፈል የ2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማስረጃ ለ. የገ/ኢ/ልማት ሚንስቴር የዕቃ ዓቅራቢነት የምዝገባ ማስረጃ ሐ. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ መወዳደር ይችላሉ ።
- ተጫራቾች ከማንኛውም የሙስናና የብክነት ድርጊቶች ነጻ የሆኑና በፌዴራልና በከልል የወጡትን የግገዢ ደንቦች በማከበር ሰነዱ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምነውበት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን በህገወጥ መንገድ ሊያራምድ የሞከረ ከጨረታው ወጪ ከመሆኑም በላይ ለወደፊቱ በሚካሄዱ ጨረታዎችን ላይ እንዳይሳተፉ ተደርጎ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረስበታል።
- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ለመቅረብ ግዴታዎቻቸውን የተወጡና የተጠየቀውን ስፔስፍኬሽን በማሟላት የወቅቱን ገበያ ያገናዘበ ዋጋ ያቀረበ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች መ/ቤቱ ባቀረበው እቃ ዝርዝር በሙሉ ወይም በሚፈልገውም የእታ ዝርዘር ላይ መጫረት ይችላል እንጂ ተጫራቹ የተወሰነ እቃ ለይቶ ማቅረብ አይችልም።
- የተወዳሪዎች ሃሳብ ሰነድ ሲቀርብ የእቃው አስፔስፊኬሽን፣ የእቃው አይነት፣የተመረተበት ሀገር ስም፤ የእቃው መለያ ሞዴል ቁጥር የተመረተበት ዓመተ ምህረት /ስፔስፍኬሽን ላይ መግለጽ አለበት።
- አሸናፊ ተጫራቾች የቅድመ ከፍያ ከጨረታው እቃ 50% ገቢ ካደረጉ በኋላ ከጠቅላላው ዋጋ 30% ብቻ መጠየቅ ይችላሉ።
- አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የእቃ አይነት የነጠላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የሚቀርበው ዋጋ የወቅቱን አካባቢ ገበያ ያገናዘበ መሆን ይገባዋል።
- የእቃው ሞዴል ወይም ስዕል ናሙና ከጫረታ ሰነዱ ጋር ይቀርባል።
- መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ጨረታ ላይ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
- አሸናፊ ተጫራች ተወዳዳሪ/ የውድድሩ ውጤት ከተነገረበት 5-10 ቀን ቀርቦ ውል ካልፈጸመ ከጨረታ መሰከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ይወረሳል።
- የጨረታው የመወዳደሪያ ሃሳብ ሰነድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በተለያዩ አንድ ፖስታዎች ከተፈላጊ መረጃዎች ጋር ተያይዞ በሰም ታሸገ ኢንቨሎፕ ይቀርባል።
- የሚቀርበው ሰነድ ሙሉ አድራሻ የተጻፈበት ሆኖ በሚመለከተው ባለስልጣን የተፈረመበትና በማህተም የተረጋገጠ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው በሸገር ከተማ ሱሉልታ ከ/ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ ቤት አንድ/1/ከ-230 እስከ 12፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ የያዘ ፖስታ ጫረታውን ከገዙበት ቀን ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ባይገኙም የጨረታው ሳጥኑ ይከፈታል።
- ሰነዱን ለመመርመርና ለመገምግም የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ መስሪያ ቤቱ ተጫራቾቹ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ ላይ መግለጫ መጠየቅ ይቻላል።
- ጨረታውን በመመርመር ሂደት ላይ የተገኘውን የሀሳብ ስህተት ማስተካከል ይቻላል። ድርጊቱ ወዲያው የመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ ላቀረበው ከፍል ይገለጽለታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የውድድር ሀሳብ መቀየር ማሻሻል ወይም ከጨረታው ውስጥ ራስን ማግለል አይቻልም።
- አሸናፊ ተጫራቶች የውል ማስከበሪያ የጨረታ ውጤት ከተነገረበት 5-10 ቀን ውስጥ ከግዢው ዋጋ ላይ 10% በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም /CPO/ በማቅረብ የግዢው ውል መፈረም ይኖርበተል።
- የጨረታው ማስከበሪያ አሸናፊው ከታወቀ ለተሸናፊው ይመለስለታል።
- ለእሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የውል ማስከበሪያውን ገቢ አድርጎ ከጨርስ በኃላ ይመለስለታል።
- አሸናፊው ተጫራች ውል ከፈጸመ በኋላ በዐ ቀን ውስጥ እቃውን አጠናቆ ማቅረብ አለበት።
- የጨረታው ዋጋ የጨረታውን ውጤት ከተነገረበት ቀን እንስቶ ዕቃውን ማስረከቢያ ቀን ድረስ ያለምንም ለውጥ መቆየት አለበት።
- ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ካሸነፈ እቃዎቹን በሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት ማውጫና ማውረጃ ችሎ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ ቤት እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የሚቀርቡት ዕቃዎች የተቀደዱ፣ የተሰበሩ፥ የተበላሹና ከአገልግሎት ውጪ ከሆነ መሥሪያ ቤቱ አይቀበላቸውም።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልም የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው:: የሰነድ መሸጫ የማይመለስ 500 ብር ብቻ ነው።
- ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 / መቶ ሺህ ብር /በባንክ በተመሰከረለት (ቼከ/ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910821521 በዚህ ስልከ ቁጥር ደውለው ሚፈልጉትን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
በሸገር ከተማ ሱሉልታ ክ/ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Tender for office supplies, cleaning materials, electronics, and furniture for sectors under the Wersebi District Finance Office, Sululta Sub-City. Bidders need valid trade licenses, tax clearance, supplier registration, and VAT registration. Bids must cover full item lists; delivery to the office warehouse is required.
