Tender Detail

Tender Details


የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለመምሪያውና ለተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር YS/C/d/NCB001/2019 ዓ/ም

 

የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለመምሪያውና ለተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ አልባሳት፣ የፅህፈት ዕቃዎች፣ የህትመት ውጤቶች፣ የህከምና እቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ ሊፍትና ጀነሬተር ጥገና ባለሙያ፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ ዊልቫላንስ እና የመኪና እጥበትና ግሪስ በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ ለመፈፀም በማስፈለጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

ሎት

 

የሚገዙ ዕቃዎች ሎት ዝርዝር

 

በሲፒኦ የሚያዝ ገንዘብ መጠን

 

ሎት 1

 

የደንብ አልባሳት

 

3,000.00

 

ሎት 2

 

የፅህፈት ዕቃዎች

 

3,000.00

 

ሎት 3

 

የህትመት ውጤቶች

 

3,000.00

 

ሎት 4

 

የህክምና እቃዎች

 

3,000.00

 

ሎት 5

 

የፅዳት ዕቃዎች

 

3,000.00

 

ሎት 6

 

የግንባታ ዕቃዎች

 

3,000.00

 

ሎት 7

 

ሊፍትና ጀነሬተር ጥገና ባለሙያ

 

3,000.00

 

ሎት 8

 

ቋሚ ዕቃዎች

 

3,000.00

 

ሎት 9

 

የመኪና ጎማ ዊልቫላንስ

 

2,000.00

 

ሎት 10

 

የመኪና እጥበትና ግሪስ

 

2,000.00

 

 

በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው

1.      የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

2.    የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት መቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

3.    የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።

4.    አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ላይ ተቀባይነት የለውም።

5.    በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በየካ ክ/ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስም በተዘጋጀው በባንክ በተመሰከረለት የባንክ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6.    የጨረታ ዋጋው በታች የሚቆይበት 60 ቀን ነው።

7.    በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።

8.    ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃ ናሙና ከጨረታ መከፈቻ ቀን በፊት መቅረብ ይኖርበታል። ተጫራቾች ሾላ ገበያ በሚገኘው፣ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

9.    ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እንዲሁም በ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ቢሮ ቁጥር 505 ይከፈታል።

10.   የጨረታው መክፈቻ ከስራ ቀናት ውጪና የክብረ በአል ቀናት ከዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል።

11.    ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

12.   መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁጥር 011 667 6482/ 011 663 9002

 

የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Yeka Sub-city Police seeks bids for goods across 10 lots: uniforms, office supplies, printing, medical items, cleaning materials, construction goods, lift/generator maintenance, fixed assets, tire services, and car washing/greasing. Bidders need valid licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
Save Tender