Tender Detail

Tender Details


በምዕራብ ወለጋ ዞን የሰዮ ኖሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ የጽህፈትና ጽዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር፣ የሞተር ብስክሌትና የመኪና ጎማዎች፣ የግንባታ ዕቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በምዕራብ ወለጋ ዞን የሰዮ ኖሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጃት ዓመት በወረዳዉ ስር ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ የጽህፈትና ጽዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር፤

የሞተር ብስክሌትና የመኪና ጎማዎች፣ የግንባታ ዕቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት። እንድሁም የተለያዩ ዕቃዎችን በጭነት መኪና ከአዲስ አበባ ደበሶ፤ ከነቀምት ደበሶ፤ ግምቢ ደበሶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማቅረብ ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸዉ

1.      ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለዉና የዘመኑን ግብር የከፈለ።

2.    የመንግስት መስሪያ ቤቶች በጨረታው ለመሳተፍ የአቅራቢነትና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣

3.    የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና ቲን ነምበር ያለዉና ማቅረብ የሚችል።

4.    ተጫራቾች የማይመለስ የጨረታ ሰነድ ብር 100.00/አንድ መቶ ብቻ/ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰዮ ኖሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዢ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5.    ተጫራቾች ዋጋ ማቅረቢያ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማኖር አለበት።

6.    ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ብር የጽህፈትና ጽዳት 3000 (ሶስት ሺህ)፣ ለኤሌክትሮኒክስ 3000 (ሶስት ሺህ ብር)፤ ለፈርኒቸር 3000 (ሶስት ሺህ ብር)፤ ለሞተር ብስክሌትና የመኪና ጎማዎች 3000 (ሶስት ሺህ) ብር፤ ለግንባታ ዕቃዎች 3000 (ሶስት ሺህ ብር)፤ ለጭነት መኪና 3000 (ሶስት ሺህ) ብር በሲፒኦ ከንግድ ባንክ፣ ከአዋሽ ባንክ፣ ከሲንቄ ባንክ እና ከኦፕሬቲቭ ባንክ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ።

7.    ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ በሁለት ፖስታ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ተብሎ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ እንዲሁም በተራ ቁጥር አንድ ላይ የተዘረዘሩትን ሕጋዊነት ማረጋገጫ አሟልቶ በእያንዳንዱ ፖስታ ማቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀዉ ጨረታ ሳጥን ዉስጥ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ በሰዮ ኖሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው።

8.    የዕቃው ናሙና መታየት የሚገባቸዉን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችል

9.    የሚቀርቡትን ዕቃዎች ጥራት የጠበቀና በተሰጠዉ እስፔስፍኬሽን መሰረት ኦርጂናል ዕቃዎች ማቅረብ የሚችል ሲሆን ጥራቱን ያልጠበቀና ኦርጂናል ያልሆነ ዕቃ ካቀረበ በራሱ ወጪ መመለስና መቀየር ግዴታ አለበት

10.   ጨረታው የሚዘጋዉ በ7/1/2019 ዓ.ም በስራ ቀን 6:00 ሲሆን የሚከፈተዉ 7/1/2019 ዓ.ም በስራ ቀን በ 8:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።

11.    ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ካልተገኙ ጨረታዉ በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል።

12.   መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው በህግም አይገደድም።

13.   አሸናፊዉ ተጫራቾች ከቀረበዉ ጠቅላላ ዋጋ 10% ለዉል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

14.   ለሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

15.   ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 ላይ የተዘረዘሩት ለጨረታ ሲቀርቡ ወዲያዉኑ የሚመለስ በእጅ ይዞ መቅረብ አለበት።

16.   የሚቀርቡ ዕቃዎች በባለሙያ ከታዩ በኋላ ርክክብ ይደረጋል።

17.   ተጫራቾች የቀረቡት ዕቃዎች ዋጋ በአንድ ቦት ተዳምሮ ጠቅላላ የጽህፈትና ጽዳት፣ ኤሌክትሮኒከስ፣ ፈርኒቸር፣ የሞተር ብስክሌትና የመኪና ጎማዎች፣ የግንባታ ዕቃዎችን፣ በደንብ ልብስ ላይ ዝቅተኛ ዋጋ ያአቀረበ አሸናፊ ይሆናል

18.   ተጫራቾች በጨረታዉ አሻናፊ ሆነዉ ሺቀርቡ ፅቃቸዉን በራሳቸዉ ማጓጓዣ እስከ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለባቸው

19.   ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ላይ አልፎ አልፎ ዋጋ መሙላት እና ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር ማሙለቱ ከልተገለጸ ይገለላል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 17 43 63 24 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ።

 

 

በምዕራብ ወለጋ የሰዮ ኖሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of office and cleaning supplies, electronics, furniture, motorcycle and vehicle tires, construction materials, and uniforms for sector offices under Seyo Nole district. Also includes freight transport from Addis Ababa, Nekemte, and Gimbi. Bidders must have valid licenses, tax clearance, VAT registration, and provide samples.
Save Tender