በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019ዓ.ም
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት-1 ቋሚ ዕቃ ( የመኪና ጎማ ፣ቪዲዮ ካሜራ እና ሞንታርቦ ) ሎት2-እስቴሽነሪ ዕቃዎች ሎት-3 የጽዳት ዕቃዎች ሎት-4 የደንብ ልብስ ሎት-5 የግብርና ዘሮች ሎት-6 የመስተንግዶ አገልግሎት ሎት-7 የኪራይ አገልግሎት (መኪና፣ሞንታርቦ፤ዲኮርእና ድንኳን ኪራይ አገልግሎት) እና ሎት-8 ጥገና አገልግሎት ( ፈርኒቸር ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
- ተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O ማቅረብ አለባቸው::
| የሎት ቁጥር | የሎት ዝርዝር ዕቃዎች | የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ በኢትዮጵያ ብር |
| ሎት1 | ቋሚ ዕቃ ( አይሲቲ ዕቃዎች ፣የመኪና ጎማዎች ፣ ጋሪዎች ፣ የካሜራ መገልገያዎች እና ሌሎች መገልገያዎች ) | 30000.00 |
| ሎት2 | እስቴሽነሪ ዕቃዎች ( የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች) | 30000.00 |
| ሎት3 | የጽዳት ዕቃዎች | 30000.00 |
| ሎት4 | የደንብ ልብስ | 30000.00 |
| ሎት5 | የግብርና ዘሮች | 5000.00 |
| ሎት6 | የመስተንግዶ አገልግሎት | 10000.00 |
| ሎት7 | የኪራይ አገልግሎት (መኪና፣ሞንታርቦ፣ ድንኳን እና ዲኮር ኪራይ) | 10000.00 |
| ሎት8 | የጥገና አገልግሎት (ፈርኒቸርና ኤሌትሮኒከስ) | 10000.00 |
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎት የማይመለስ ብር 400 / አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 305 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት ዋጋውን የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋጋውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው በክኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10%ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ እና በተጨማሪ የቢሮ መስተንግዶ አገልግሎት ለምትጫረቱ ነጋዴዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሽነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታው ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስ ሆነ የመጨመር መብቱ የጠጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ከመገናኛ ወደ 24 ቀበሴ ኮከብ ህንፃ አጠገብ ወረዳ 05 አስተዳደር በመቅረብ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 ፋ/ጽ/ቤት መጠየቅ ይቻላል፡፡
ስልክ ቁጥር፡-09-05-60-96-79
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement across 8 lots: ICT equipment, vehicle tires, stationery, cleaning supplies, uniforms, agricultural seeds, hospitality services, rental services (vehicles, tents, decor), and furniture repair. Bidders need valid licenses, tax clearance, and supplier registration.
