Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤ
  • Address አዲስ አበባ ኢትዮጵያ, Phone: 0913247806
  • Website
  • Deadline24 Sep 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300, 200, 400, 200, 200 (per lot)
  • opening dateየጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በየሎቱ ይለያያል።
  • Categories Office Supplies And Services , Printing And Publishing , Vehicle tire

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብረኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን ለመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ/ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ በጀት እና በሴፍትኔት በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብረኤል ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን ለመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ/ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ በጀት እና በሴፍትኔት በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የግዥው አይነት የጨረታ መግዣ ብር የጨረታ ማስከበሪያ አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ
1 የፅህፈት መሳሪያ 300 90000 ለእቃ አቅርቦት ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀን ሲሆን ብ 21 ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል እና የሴፍትኔት የጽህፈት መሳሪያ አቅርቦት ለ 30 ቀን ሲሆን በ31 ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል።ሁሉም ግዥዎች 21ኛው ቀን እና 31ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል።
2 የህትመት ስራ 200 10000
3 የመኪና ጎማ 400 90000
4 የፅዳት እቃ 200 20000
5 የፅህፈት መሳሪያ በሴፍትኔት በጀት 200 20000

በዚህ ጨረታ መሳተፍ የምትችሉ በአንድ ሎት/ምድብ ያሉት የአቅርቦት እቃዎች ዋጋቸው ከ500,000/አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ የሆኑ እቃዎች ላይ መወዳደር የሚችሉ የቫት ተመዝጋቢ የንግድ ድርጅቶች ብቻ ሲሆኑ ከብር 500,000/ አምስት መቶ ሺህ ብር /በታች የሆኑት የአቅርቦት እቃዎች ላይ መወዳደር የሚችሉ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑም ያልሆኑም ድርጅቶች የሚወዳደሩ ሲሆን በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣የታደሰ፣አግባብነት ያለው ንግድ ስራ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነበር) እና የቫት ተመዝጋቢ ማረጋገጫ ማስረጃ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡

የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚያቀርቡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ መሰረት በመሙላት አንድ አርጅናል በማሸግ በመ/ቀ/ገ/ወ/ገ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የአቅርቦት እቃ የሚያቀርቡበትን ዋጋ መሙላት አለበት
  2. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ ዝርዝር ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ፣በፍሉድ የተሰረዘ ወይም ለማንበብ አስቸጋሪ የሆነ ሰነድ የተከለከለና ከጨረታ የሚያሰርዝ ነው፡፡
  3. ለጨረታ የሚያስፈልገውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ያላቀረቡ ተጫራቾች በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
  4. የተጫራቾች ፖስታ በሰም ባለመታሸጉ ከጨረታ አያሰርዝም፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያስያዙት በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ/በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መሆን አለበት ::
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነቱ ተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የአቅርቦት እቃ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል ያልፈጸሙ እንደሆነ ግዥ ፈጻሚው አካል የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው ፡፡
  8. ናሙናን በተመለከተ ፅ/ቤቱ የፕሪንተር ወረቀት ፣የፕሪንተር ቀለም ፣ ፅ/ቤቱ ናሙና ስለሚያቀርብ ከናሙናው ያነሰ እቃ የማንቀበል ሲሆን ተወዳዳሪዎች ናሙናውን በማየት ዋጋ መሙላት አለባቸው ሌሎቹን እቃዎች አንደኛ ደረጃ ኦርጂናል እቃ መቅረብ አለበት፡፡

ስልክ ቁጥር 0913247806 0116736550

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ቀያ ገብርኤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for the supply of office supplies, printing services, vehicle tires, and cleaning items under regular and safety-net budgets. Bidders must hold valid licenses, pay taxes, and provide VAT registration where required.
Save Tender