Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ አርሲ ዞን የቆሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ምዕራብ አርሲ ዞን ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916107688
  • Website
  • Deadline06 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/
  • opening dateበዛው እለት 4፡30 ሰዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Electrical And Electromechanical , Office Supplies And Services

በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የሲራሮ ወራዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች 1ኛ ዙር ግዥ ለ 1ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ሰነድ በ2019 የበጀት ዓመት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም፦


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የሲራሮ ወራዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች 1ኛ ዙር ግዥ ለ 1ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ሰነድ በ2019 የበጀት ዓመት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም፦

  • አላቅ ዕቃዎች /ጽህፈት መሳሪያዎች
  • ኤሌትሮኒክስ
  • ፈርኒቸር
  • የፅዳት ዕቃዎች
  • የደንብ ልብስ

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጸውን በግልጽ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸውን ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። መመሪያ/ መስፈርት በመከተል ይህን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን 2018/2019 ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ቫት ከፋይ የሆኑ TIN Number ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች ወደ ጨረታው ሂደት ከገባ በኋላ በሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሀሳቤን ቀይሬአለው ማለት አይቻልም፡፡
  3. ማንኛውም ዕጩ ተወዳዳሪ የጨረታውን ሂደት ለማስተጓጐል ቢሞክር ከጨረታው ውጭ እንዲሆን ተደርጎ ወደ ፊት በሚደረገው የመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ የሚደረግ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ይሆናል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ እንዲችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ እና በንግድ ፍቃዳቸው ዘርፍ ብቻ ነው መወዳደር የምትችሉት፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለያንድአንዱ የግዥ መደብ ብር 5000/አምስት ሺህ ብር ብቻ, በባንክ በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት፡፡ ነገር ግን በካሽ ከሆነ በሲራሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር1000289568418 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ተደርጎ computer generated slip መቅረብ አለበት፡፡
  7. ተወዳዳሪ ድርጅቶች የዕቃ ጥራት ደረጃቸው አስቸጋሪ የሆኑ የዕቃ ዓይነቶች መሥሪያ ቤታችን ቀድሞ ስላዘጋጃ ለምሳሌ የኮምፒተር ወረቀት፣ እስከሪብቶዎች፣ ኬንት፣ ሶፍት፣ ኡሁ የኮምፒተር ቀለም፣ ኦርጅናል የቆዳ ወጤቶች ፣ቦርሳዎች እና ሌሎችም ተወዳዳሪ ድርጅቶች ይህን ናሙና መሠረት በማድረግ ብቻ የምንቀበል መሆኑን በጥበቅ እናሳስባለን፡፡
  8. አሸናፊ ድርጅት ዕቃውን ጭነው እስከ መ/ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  9. ተጫራች ዕቃው የተሰራበትን የተመረተበትን ሀገርና የጥራት ደረጃ የመስራት አቅሙን እንዲሁም ሞዴሉንና የተመረተበትን ዓ.ም መግለጽ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. ተጫራቶች የጨረታ ዋጋውን መሙላት ያለባቸው በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት ፡፡ እንዲሁም እያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ በራሳቸው ሰነድ ላይ የሚሞላ ለስራችን አመቺ ስለማይሆን ተቀባይነት የለውም፡፡
  12. ጽ/ቤታችን የሚያጫርታቸውን የአንዱ ዋጋ ሲሆን አሸናፊው የሚፈልገውን የዕቃ ብዛት ማዘዝ ይችላል፡፡
  13. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥራቸውን ፋክስ ቁጥራቸውን በትክክል ፅፈው መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  14. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት የጨረታ ዋጋው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ 60 ቀናት ወይም ሁለት ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
  15. መ/ቤቱ ጨረታውን ገምግሞ ለማሳለፍ ወይም ውድቅ ለማድረግ የሚጠቀምበት ዘዴ እንደ ዕቃው አይነት ወይም የሚፈለገው አገልግሎትን መሰረት በማድረግ ጥራትን ወይም ዋጋን ከግንዛቤ በማስገባት ተወዳዳሪዎችን አሸናፊ ወይም ውድቅ የሚያደርግ ሲሆን ሁለት እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ በብዛት ላሸነፈው የሚሰጥ ይሆናል፡፡
  16. የሰነዱ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን 22/12/2018 እስከ 25/01/2019 ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ 26/01/2019 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኘበት በዛው እለት 4፡30 ሰዓት ላይ በሲራሮ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡
  17. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሲራሮ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤት ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በሲራሮ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000289568418 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ቢሮ ቁጥር 07 ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ተወዳዳሪ ድርጅቶች ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀለት የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት የሰነዱን ሽያጭ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ማስገባት ይችላል ፡፡
  18. የጨረታ ውል ከጨረታ ሰነድ ጋር ስለሚሸጥ በውል መሰረት ጨረታውን ያሸነፈው ነጋዴ ለውሉ ተገዥ መሆን አለበት ፡፡
  19. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  20. አሸናፊ ድርጅቶች ካሸነፉ ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር1000289568418 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ወይም በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት ፡፡

0994442023/0911140912

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ አርሲ ዞን የሲራሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for first-round procurement of office supplies, electronics, furniture, cleaning items, and uniforms for sector offices in Siraro Woreda, West Arsi Zone. Bidders must hold valid trade licenses, pay taxes, and provide VAT/TIN certificates.
Save Tender