በየካ/ከ/ከ ወረዳ 02 አስተዳደር የፋ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዕቃዎች እና ጌጣጌጥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ/ከ/ከ ወረዳ 02 አስተዳደር የፋ/ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት አላቂ የቢሮ ዕቃ (አስቴሽነሪ)፣ ቋሚ ዕቃ (የአዳራሽ/ኮንፈረንስ ወንበር፣ የደንበልብስ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ህትመት አገልግሎት፣ የዲኮር ስራ፣ ሞንታርቦ፣ ጄኔሬተር እና ወንበር ኪራይ አገልግሎት፣ የጥገና (የአይቲ) ስራ አገልግሎት፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እና ጌጣጌጥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በሚሰጠው አገልግሎት ከመ/ቤቱ ጋር ውል ወስዶ በሚፈለገው ሰዓት ማቅረብ እና አገልግሎቱን መስጠት የሚችል፡፡
- በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት የጨረታ መመሪያ፣ የዕቃና አገልግሎት ስፔስፍኬሽን አጠቃሎ የያዘ የጨረታ ሰነድ በአካል መጥተው ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብቻ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ በሚሆኑበትን ዕቃ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በጥሬ ማስያዝ የሚችል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት የሚከፈት ሲሆን የሚከፈትበት ቀን እሁድ እና ቅዳሜ /የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በተመለከተ የደንብ ልብስ 13.000 (አስራ ሶስት ሺህ)፣ እስቴሽነሪ 5,000.00 (አምስት ሺህ)፣ የፅዳት ዕቃ 5,000.00(አምስት ሺህ)፣ ትራንስፖርት 5,000(አምስት ሺህ)፣ ህትመት 5,000.00(አምስት ሺህ)፣ ጥገና አገልግሎት 3,000.00(ሶስት ሺህ)፣ የመኪና መለዋወጫ 5,000.00(አምስት ሺህ)፣ የሰራተኞች ካፌ አገልግሎት 5,000.00 (አምስት ሺህ) እና የቢሮ መስተንግዶ አገልግሎት 3,000.00 (ሶስት ሺህ) CPO ብቻ ማስያዝ እንዳለባቸው እየገለፅን በድጋፍ ደብዳቤ ለምታመጡ ነጋዴዎች የምታስገቡት ዕቃ በሀገር ውስጥ ለሚመረቱ ዕቃዎች፣ ለትራንስፖርት፣ ለህትመትና ለጥገና እና ለመስተንግዶ አገልግሎት የምናስተናግድ ሲሆን ከሀገር ውጪ ለሚመረቱ/ለሚገቡ ምርቶች በድጋፍ ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ለሚያቀርቡት ዕቃ ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ፈረንሳይ ለጋሲዎን ማዞሪያ አደባባይ 100 ሜትር ገባ ብሎ የካ ከ/ከ ወረዳ 02 አስተዳደር አንደኛ ፎቅ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111548903 መደወል ይችላሉ፡፡
በየካ ክፍስ ከተማ ወረዳ 02 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
The Bole sub-city District 02 Administration Finance Office seeks bids for office supplies, furniture, cleaning materials, transport, printing, decoration, IT maintenance, hospitality, staff cafe, vehicle spare parts, and ornaments for the 2019 budget year. Bidders must have a renewed trade license, VAT registration, supplier registration, and provide samples before bid opening.
