Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መግዛት ይፈልጋል


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2019

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት በወረዳው ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፡ ሎት 2 የእንስሳት መድሃኒትና ቁሳቁስ ፡ ሎት 3 የቢሮ መገልገያ፡ ሎት 4 የጽዳት እቃ፣ ሎት 5 የመኪና ጎማ፡ ሎት 6 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 7 ህትመት እና ሎት 8 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በየንግድ ዘርፉ የተሰማሩ ሆነው መጫረት የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች፤

  1. ዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው፤
  5. የግዥ መጠኑ ከብር 200000/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት ተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  6. የእቃው አይነት ዝርዝር መግለጫ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ገንዘቡን በመከፈል የጨረታ ሰነዱን እንገልጻለን፡፡
  7. ተጫራቾች በምትጫረቱበት ሎት ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ለጽህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ 60000 ስልሳ ሺህ ብር/ ለቢሮ መገልገያ 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ ለጽዳት እቃ 4000 /አራት ሺህ ብር/ ለእንስሳት መድሃኒትና ቁሳቁስ ግዥ 16000/ አስራ ስድስት ሺህ ብር/ ፈርኒቸር 10000 /አስር ሺህ ብር/ ኤሌክትሮኒክስ 50000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የመኪና ጎማ 6000/ስድስት ሺህ ብር/ ህትመት 3000/ ሶስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ ወይም ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት ታሽጎ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30/ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 001 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 3፡31/ሶስት ሰአት ከሰላሳ አንድ ደቂቃ ተዘግቶ 4:00/አራት ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 001 ውስጥ ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሔራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. በጨረታው ተሳታፊዎች ፖስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙያው ላይ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ወይም ህጋዊ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. በጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ካለ ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  13. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ይሆናል፡፡
  14. መ/ቤቱ እቃዎችን 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡ ናሙና ሰሚያስፈልጋቸው እቃዎች በተቋሙ በአካል በመምጣት በማየት መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ አሸናፊውም ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ወረዳው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  15. ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 0116880408 ወይም 0116880330 ላይ መደወል ይችላል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of office supplies, veterinary drugs, cleaning materials, vehicle tires, electronics, printing, and furniture across 8 lots for district offices. Bidders need valid licenses, TIN, tax clearance, and VAT registration for purchases over 200,000 birr.
Save Tender