Tender Detail

Tender Details

  • Company የሮቤ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
  • Address በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0966696974
  • Website
  • Deadline12 Sep 2026, 9:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 (አምስት መቶ) (የማይመለስ)
  • opening dateበዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Electrical And Electromechanical , Office Supplies And Services

በባሌ ዞን የሮቤ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከስ፣ ፕላስቲክ መገጣጠሚያዎች፣ ጂአይ መገጣጠሚያዎች፣ የፕላስቲክ ቧንቧዎች፣ የመኪና ጎማዎችና መለዋወጫ፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ እና የውሃ ጥራት መጠበቂያ ኬሚካሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

በባሌ ዞን የሮቤ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒከስ፣ ፕላስቲክ መገጣጠሚያዎች፣ ጂአይ መገጣጠሚያዎች፣ የፕላስቲክ ቧንቧዎች፣ የመኪና ጎማዎችና መለዋወጫ፣ የሰራተኛ የደንብ ልብስ እና የውሃ ጥራት መጠበቂያ ኬሚካሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል በተሰማራበት ዘርፍ ህጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
  2. ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ የሚያቀርብ ተጫራች የውሃ ፈንድ ክፍያ 0.5% መከፈል ይኖርበታል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመከፈል ከሮቤ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 2% ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጨረታው ሰነድ በተጠቀሰው መሰረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በሙሉ የመጫኛና የማጓጓዣ ወጪውን በመቻል መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  9. የእቃዎቹን ዋጋ መስሪያ ቤቱ የሚከፍለው ተጫራቹ ለማቅረብ ውል የፈረሙባቸውን እቃ ሙሉ በሙሉ በንብረት ክፍላችን ገቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ሲቀርብ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፍቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው በ10 ቀን ውስጥ መ/ቤት ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው፡፡
  11. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አይራዘምም፡፡

በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር -0966696974፣ 0904449498 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሮቤ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Robé City Water and Sewerage Service Enterprise seeks bids for office supplies, cleaning materials, electronics, plastic and GI fittings, plastic pipes, vehicle tires and spare parts, staff uniforms, and water treatment chemicals. Bidders must hold a valid, renewed trade license with paid taxes.
Save Tender