በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ2019 በጀት በ1ኛ ሩብ ዓመት
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ2019 በጀት በ1ኛ ሩብ ዓመት
በሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎችን፣
በሎት 2 የተለያዩ የፅዳት እቃዎችንና ልዩ ልዩ አላቂ እቃዎችን፣
በሎት 3 የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን፤
በሎት 4 የጀነሬተር መለዋወጫ ዕቃዎችን እንዲሁም
በሎት 5 የተለያዩ የግንባታና የቧንቧ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራች ማሟላት የሚገባቸው
1. ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤
5. የዘመኑን ግብር የከፈለ ከኢትዮ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን/በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
6. ተወካይ ከሆነ/ ከሆነች/ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
7. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፣
8. ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ቫት ሳይጨምር በመሙላት በዘርፉ ድምር ከተሰራ በኋላ የቫት ድምር ለብቻ መቀመጥ አለበት።
9. ተጫራች የአንድ ዋጋ ከሞላ በኋላ ወደ ጎን አባዝቶ እና ወደ ታች ደምሮ ማስቀመጥ ይኖርበታል።
10. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር በተናጠል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ እየሆነ ይመረጣል።
11. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ስርዝ ድልዝ ካለ እና ፍሉድ ከተጠቀሙ ሰነዱ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
12. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል። ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ ኮፒውን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ እንዲሁም በየዘርፉ ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻ ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽጎ የሚወዳደርበትን ዘርፍ በመፃፍ ማቅረብ አለበት። በዚህ መሰረት ሶስቱንም ፖስታዎች ለየብቻ ሳያሽግ በአንድ ላይ አሽጎ ቢመጣ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
13. ለጨረታ ማስከበሪያ ካቀረቡት ዋጋ ልክ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
14. የጨረታ አሸናፊዎች ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
15. የጨረታ ሰነዱን ከማሰልጠኛ ት/ቤቱ ፋይናንስ ዴስክ በስራ ቀንና ሰዓት ከ23/12/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 02/13/2018 ዓ.ም ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
16. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በ03/13/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ በማ/ት/ቤቱ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ሰነዱን ማስገባት አለባቸው፣ በዚሁ ቀን 03/13/2018 ዓ.ም ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በማ/ት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
17. አሽናፊ የሆነው ተጫራች ማ/ት/ቤቱ በሚሰጠው የዕቃ አቅርቦት ትዕዛዝ መሰረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል እና በማ/ት/ቤቱ የጥራት ኮሚቴ ጥራቱን አረጋግጦ ማስረከብ አለበት። የጥራት ኮሚቴው ካልተቀበለው ቀይሮ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
18. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሪጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።
19. ማ/ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
20. ጨረታውን አሸናፊ ከሆነ ድርጅት ማ/ት/ቤቱ በጀቱን በማረጋገጥ በዘርፋ 20% የመቀነስም ሆነ 20% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
21. በዚህ ማስታወቂያው ያልተገለጹ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መምሪያ መሰረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፣
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 760 0018 በስራ ሰዓት ደውሎ ማረጋገጥ ይችላሉ።
የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማ/ት/ቤት
