የጋሞ ዞን ፋይናንስና ኘላን ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት 1/ የጽሕፈት መሣሪያ 2/ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች 3/ የጽዳት ዕቃዎች 4/ የኤሌክትሪክ ሞተር ሣይክል 5/ ደንብ ልብስ 6/ ፈርኒቸር 7/ የሞተር ሣይከል ጐማ 8/ የግንባታ ዕቃዎች 9/ ሕትመት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋሞ ዞን ፋይናንስና ኘላን ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት 1/ የጽሕፈት መሣሪያ 2/ ኮምፒውተርና ተዛማጅ ዕቃዎች 3/ የጽዳት ዕቃዎች 4/ የኤሌክትሪክ ሞተር ሣይክል 5/ ደንብ ልብስ 6/ ፈርኒቸር 7/ የሞተር ሣይከል ጐማ 8/ የግንባታ ዕቃዎች 9/ ሕትመት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና በአቅራቢት የተመዘገቡ፣
- የንግድ ፍቃድና ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 15 ባሉት ቀናት ብር -200.00/ሁለት መቶ ብር/ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሣብ ቁጥር 1000038613263 በማስገባት እና የባንክ አድቫይስ ይዘው ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኙን በማሳየት ከጋሞ ዞን ፋይናንስና ኘላን ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (BD security) ለእያንዳንዱ 80,000/ሰማኒያ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የከፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ከሬዲት በዋናው የሕጋዊነት ሰነድ እንቬሎፕ ውስጥ አስገብተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት በፖስታ በጥንቃቄ በማሽግ የሚወዳደሩበትን ዓይነት በፖስታው ላይ በመለየት በግዥና ንብረት አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ያለተጨማሪ ወጪ እስከ ቢሮአችን በማምጣት የማስረከብ ኃላፊነት አለበት።
- የጨረታ መከፈቻ በበዓላት ወይም በሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር-046-881-3338 በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጋሞ ዞን ፋይናንስና ኘላን ልማት መምሪያ
✨ messages.ai_summary
The Gamo Zone Finance and Planning Department seeks bids to procure office supplies, computers and accessories, cleaning items, electric motorcycles, uniforms, furniture, motorcycle tires, construction materials, and printing services. Bidders must hold a valid trade license, tax clearance, VAT registration, and supplier registration, and submit required documents.
