Tender Detail

Tender Details

  • Company የሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: 0113662199 (0913658563)
  • Website
  • Deadline15 Sep 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300.00(ሶስት መቶ ብር)
  • opening dateበ16ኛው ቀን 4፡30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Vehicle

የሰበታ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሎትኪ የጽሕፈት መሣሪያዎች, ጽዳት እቃዎች፤ አላቂ እቃዎች፣ ደንብ ልብሶች: ሎት 2 የመኪና ጎማዎችን፤ ኤሌክትሮኒከስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሰበታ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ሎትኪ የጽሕፈት መሣሪያዎች, ጽዳት እቃዎች፤ አላቂ እቃዎች፣ ደንብ ልብሶች: ሎት 2 የመኪና ጎማዎችን፤ ኤሌክትሮኒከስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል።

  1. ተጫራቶች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደስ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብርአጠናቀው ስለመከፈላቸው በቂ ማስረጃ (ከሊራንስ) ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከገቢዎች ባለሥልጣን በተወከለው ሠራተኛ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00(ሶስት መቶ ብር) ወደ ሲንቄ ባንከ ሂሳቢ ቁጥር በSebeta Sub city Finance office "A’’ 1064814111214 ገቢ በማድረግ ከፍለ ከተማ ገቢዎች በመሄድ ወደ ደረሰኝ በማስቀየር ዘወትር በስራ ሰዓት በሰበታ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት መግዛት ይቻላል።
  3. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎቶች በተዘጋጀው ሰነድ ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር) በባንከ በተመሰከረለት CPO ብቻ በሰበታ ከፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋርአያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል። ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት።
  6. ለጨረታ በሚያቀርቡት በእያንዳንዱ የሰነዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ስምና አድራሻ የሚገልጽ ሕጋዊ ማህተምና ፈርማ መስፈር አለበት።
  7. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችዋል።
  8. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱ በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል።
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ከስቶክ ወይም ከራሳቸው ስቶር መሆን ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት።
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ የሎት አንድ(1)2 ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው።
  12. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።
  13. ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል።
  14. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113662199 (0913658563)

የሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for office supplies, cleaning materials, uniforms, vehicle tires, electronics, and furniture. Bidders need valid trade licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier certification. Goods must be quality-checked and delivered to the office.
Save Tender