Tender Detail

Tender Details


የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውልና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን፤


የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የፕሪንተር ቀስሞች እና የንጽህና/የጽዳት ዕቃዎች ግዥ

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር፣ ኦ.ደ.ዱ.እ.ድ- 02/2019

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውልና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን፤

  1. ሎት 1፡ የጽህፈት መሣሪያዎች
  2. ሎት 2፡ የፕሪንተር ቀስሞች
  3. ሎት 3፡ የንጽህና/የጽዳት ዕቃዎች

በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ደፍሏል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው ላይ በሙሉም ሆነ በከፊል እንዲሳተፉ መ/ቤቱ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር ከፍለው በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ በጨረታ ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) ብር በመከፈል፣ አዲስ አበባ ከተማ ቀበና አይል ሊቢያ ከፍ ብሎ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት፣ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በማየት እያንዳንዱን ዕቃ የሚያቀርብበትን ዋጋ በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) ከታወቀ ባንክ በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ስም ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና (Bank Gurantee) በማሠራት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብና ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ጨረታው መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለጸው አድራሻ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ናሙና ለተጠየቀላቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለተጨማሪ መረጃ - ከታች የተገለጸውን ስልክ ቁጥር በመደወል ወይም በፋክስ፣ በጽሑፍ መጠየቅና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ፡-

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07
ስልክ ቁጥር፡- 011-122-00-20/011-124-02-58

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት

✨ messages.ai_summary
Oromia Forest and Wildlife Enterprise invites bids for office supplies, printer cartridges, and cleaning materials across three lots. Eligible bidders must hold a renewed trade license, tax clearance, and VAT registration. Bids may cover all or part of the lots.
Save Tender