በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቱሉ ኤጀርሳ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 001-2017 ዓ.ም
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቱሉ ኤጀርሳ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
ሎት 1 የደንብ ልብስ-የሲፒአ መጠን 25,000.00
ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች -የሲፒኦ መጠን 40,000
ሎት 3 የጽዳት እቃ የሲፒአ መጠን 30,000
ሎት 4 ቋሚ የቢሮ እቃዎች ------ የሲፒአ መጠን 45,000
ሎት 5 የመኪና ጎማና ጌጣጌጦች ------ የሲፒኦ መጠን 5,000
ሎት 6 ሞንታርቦና ዲኮሬሽን ኪራይ ------ የሲፒኦ መጠን 3,000.00
ሎት 7 ህትመት ሥራዎች -------- 5,000
ሎት 8 ሕዝብና የጭነት ትራንስፖርት -------
ሎት 9 የቢሮ እቃዎች ጥገና --------
ሎት 10 የጉልበት ሥራዎች --------
ሎት 11 መስተንግዶ
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች አቅራቢዎች
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
- የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በእያንዳንዱ ሎት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት 7 በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ (ኤንቨሎፕ) ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በፋይናንስ ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸውና ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች እንዲሁም ለቋሚ እቃዎች ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የፍላጎት መግለጫ መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አቅራቢዎች ለተወዳደሩበት እቃዎች ውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- አምራች የሆናችሁ አቅራቢዎች ካደራጃችሁ አካል ተቋም በሚመለከተው አካል የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ እና አምራች ስለመሆናችሁ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣትት ችላላችሁ፡፡ አምራች ያልሆናችሁ አቅራቢዎች በዋስትና ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከሻት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል
- የዘገየ ተጫራችና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከጋርመንት ወደ አትክልት ተራ አለፍ ብሎ ከአትክልት ተራ ወደ አባ ገዳ መንገድ ገባ ብሎ፡፡
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቱሉ ኤጀርሳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
