በመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቶችና መስክ ጽ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ነገሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቶችና መስክ ጽ/ቤቶች
- የጽሕፈት መሣሪያ
- የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች
- የጽዳት ዕቃዎች
- ደንብ ልብስ
- ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
- ለስልጠና መስተንግዶ
- የሕትመት ሥራ
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማና ካለመዳሪያ ግዥ
- ማሽነሪ ጥገና
- የአጥር እና የቤት ጥገና
- የደንብ ልብስ ስፌት
- የጭነት አገልግሎት
- የተሽከርካሪ እና ሞተር ሳይክል ጥገና የእጅ ዋጋ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በአገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ከተ.ቁ 7.10.12.13 በስተቀር ለእያንዳንዱ ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ) በጥሬ ብር ወይም በሰርቲፋይድ ቼክ (CPO) ለማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 7 (ሰባት) በመውሰድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡00 ሰዓት የጨረታ ሠነድ ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በሁለት ኮፒ በማሸግ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ8፡15 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜ/ እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት በጽዳት ዕቃዎች፣ በጽሕፈት መሳሪያዎች፣ በቋሚ አላቂ ዕቃዎች እና በደንብ ልብስ ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ላይ የዕቃውን ናሙና በፎቶ ግራፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- ተጫራቾች ባሸንፉት የዕቃ ዋጋ ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ የአሰራር ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ፊት ለፊት ወጋገን ሆቴል አጠገብ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0576612054/0576615178
በመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት
