የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስራ አመራር ተቋም በተቋሙ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤ/ጉ/ክ/መ/ ስራ አመራር ተቋም በተቋሙ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በዚሁ መሰረት ለመወዳደር የምትፈልጉ- ሎት 1 (አንድ) ለሰልጣኞች የምግብ ዝግጅት የሚውል የምግብ ጥሬ ዕቃዎች (እህል)፣ ሎት 2 (ሁለት) ለስልጠና አገልግሎት የሚውል የምግብ ጥሬ ዕቃ (የባልትና ውጤቶች)፣ ሎት 3 (ሶስት) ለሰልጣኞች የምግብ ዝግጅት የሚውል የምግብ ጥሬ ዕቃዎች አትክልትና ስራስር፣ ሎት 4 (አራት) ለሰልጣኞች የምግብ ዝግጅት የሚውል የምግብ ጥሬ ዕቃዎች የበሬ ሥጋ ለሙሲሊም እና ለክርሲቲያን የሚሆን ሎት 5 (አምስት) ለተቋሙ ሰልጣኖች መጠጥ አገልግሎት የሚውል የታሸገ ውሃ፣ ሎት 6 (ስድስት) ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የጽህፈት መሳሪያ/፤ ሎት 7 (ሰባት) ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች /የጽዳት እቃዎች/ ሎት 8 (ስምንት) ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 9 (ዘጠኝ) ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል የህትመት ስራ፣ ሎት 10 (አስር) ለተቋሙ ሰራተኞች የስራ ልብስ (ደንብ ልብስ)፣ ሎት 11 (አስራ አንድ) ለሁለገብ አገልግሎት የሚውል የውሃና የኤሌክትሪክ መለዋወጫ እቃዎች (ህንጻ መሳሪያ) ሎት 12 (አስራ ሁለት) ለተቋሙ መኪኖች አገልግሎት የሚውል የቀላል እና የከባድ መኪና ጎማ፣ ሎት 13 (አስራ ሶስት) ለተቋሙ ሰልጣኞች ምግብ ዝግጅት የሚውል የምግብ ቤት ዕቃዎች ሎት 14 /አስራ አራት/ ቀላል ተሽከርካሪ /የጭነት ባጃጅ እና ሞተር ሳይክል/ ሲሆን በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ለመሳተፍ የምትፈልጉ።
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ፣ የሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከቤኒሻንገል ጉሙዝ ክልል መንግስት ስራ አመራር ተቋም አሶሳ አምባ አምስት ከግዥ እና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 ይህ ማስታወቂያ በወጣበት የአየር ላይ ከዋለበት) ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በማቅረብ መግዛትና መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው በመፈረም ማህተም በማድረግ (በመምታት) ዋናው (ዋጋ የሞሉበት) እና 1 ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተዘጋጀው ቢሮ በቀረበው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው 16ኛው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በቀጣይ የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚህ ቀን ከረፋዱ በ5:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ (bid bond) ወይም ሲፒኦ (cpo) በእያንዳንዱ ሎት ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በጥሬ ወይም በቼክ በአድራሻችን በቤ/ጉ/ክ/መ/ አመራር ተቋም ስም ተሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ተቋማችን ያዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ሳይለወጥና ሳይነካካ በዚሁ ሰነድ ላይ ወይም በራሳቸው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ በትክክል ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ ቅሬታ ካላቸው ለቤ/ጉ/ክ/መ/ሥራ አመራር ተቋም በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- 0910196578/ 0912400901/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቤ/ጉ/ክ/ሥራ አመራር ተቋም
አምባ 5
