በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የወንጪ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሰራተኛ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ልዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የወንጪ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሰራተኛ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ልዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የቫት ቲኦቲ (TOT) ተመዝጋቢዎች የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7,000 (ሰባት ሺህ) ብር በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ድርጅቶች ወይም ግለሰብ ነጋዴ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 – 10፡00 ሰዓት በወንጪ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቀጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ስለ ጨረታው ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ በመውሰድ ለእያንዳንዱ ዕቃዎች በሚያቀርቡበት ዋጋ ላይ ቫትን አካቶ በመዘርዘር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጎ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 4 እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል። 16ኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚካሄድ ይሆናል። ተወዳዳሪዎች ያሸነፉበትን ዕቃ የሚያቀርቡት ወይም የሚያስረከቡት ወንጪ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ይሆናል፡፡ ፍርድ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
አድራሻችን፣
ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ሊበን ከተማ
ስልክ ቁጥር 0113160013, 09-10-87-06-42, 09-20-58-19-57, 09-06-13-11-23 ወንጪ ወረዳ ፍርድ ቤት
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የወንጪ ወረዳ ፍ/ቤት
