በኢሉአባቦር ዞን ሐሉ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ላሎት መ/ቤቶች ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል መሣሪያዎች፣ ፈርኒቸር፣ ጎማና ካለመዳሪያ፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የጽሕፈት መሣሪያዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉአባቦር ዞን ሐሉ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ላሎት መ/ቤቶች ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል መሣሪያዎች፣ ፈርኒቸር፣ ጎማና ካለመዳሪያ፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የጽሕፈት መሣሪያዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ እንዲሁም ለመንገድ ጥገና ሥራ የተለያዩ ማሽኖችን ስሪታቸው እ.አ.አ 2013 ወዲህ ሲኖትራክ፡ ፒካፕ ቶዮታ፣ ደብል ጋቢና ለሳይት ሥራ አገልገሎት የሚውል፤ ሩሎ ባለቫይብሬተር፣ ግሬደር፣ እስካቫተር፣ ሻወርትራክ፣ ዶዘር እና ሎደር አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል እና የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡
- በንግድ ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበ፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ በሲፒኦ /cpo/ ብቻ ለእያንዳንዱ ዶክመንት ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ /cpo/ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ቀርቦ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነና ዕቃዎቹን በራሱ ሙሉ ወጪ በታዘዘ በ15 ቀን ውስጥ እስከ ጽ/ቤቱ ማቅረብና ቆጥሮ ማስረከብ አለበት፡፡
- ተጫራቹ የዕቃውን ሞዴል ባልተገለጸበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ አብራርቶ መግለጽ አለበት፡፡
- ተጫራቹ የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- በፈርኒቸር ዕቃዎች ላይ የምትወዳደሩ ድርጅቶች የፈርኒቸሮችን ዲዛይን ከዋጋው ጋር ማቅረብ እና ካሸነፈ ገጣጥሞ ማስረከብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቹ ለሚያቀርባቸው የደንብ ልብሶች እና ለመ/ቤቱ አስፈላጊ ለሆኑ ዕቃዎች ሳምፕል /ናሙና/ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቹ የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ተጠናቆ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሐሉ ወረዳ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 700.00 /ሰባት መቶ/ ብር ከሐሉ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዢ ክፍል በመግዛት የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው።
- የሚወዳደሩበትን ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
- ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ፍቃዱንና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን የሚገልጽ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ሲፒኦ /cpo/ ለየብቻ 5 /አምስት/ ፖስታዎችን ማሸግ አለባቸው።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው ሣጥን በግዥ ክፍል ውስጥ ክፍት መሆኑን አውቃችሁ እስከ 15ኛው ቀን ፖስታዎችን የሥራ ቀናት በፈለጋችሁት ቀን ማስገባት ትችላላችሁ።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሽኑን ማምጫ እና መመለሻ እስከ ሐሉ ወረዳ መንገድ እና ሎጅስቲክስ ጽ/ቤት እና ሥራ ቦታ (ሳይት) ማስገባት እና ከአንድ ቦታ (ሳይት) ወደ ሌላ ቦታ (ሳይት) ሥራ የሚሠራበት ሳይት ማቅረብ ማንቀሳቀስ በራሱ ወጪ የሚችል፡፡
- የማሽኑ የማስጫኛ እና ማውረጃ እና ነዳጅ በአሸናፊ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸኑን በፈጸሙት ስምምነት መሰረት ካላቀረቡ ለሥራቸው አፈፃፀም ያስያዙት 10 ለመንግሥት ገቢ ይሆናል
- ማሽኑ ቢበላሽ በ 5 ቀን መካከል ቀይሮም ይሁን አሠርቶ የባለንብረቱ ይሆናል
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ፡- 0911013596 / 0910873922 / 0922003180
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር በኢሉባቦር ዞን የሐሉ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
