Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሣሪያ፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቐሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሣሪያ፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቐሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. በዚህ ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ያለው የ2017/2018 የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  2. አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በአስር ቀን ውስጥ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በሙሉ ኩዩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል።
  3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የያዘ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000036504416 በመክፈል የባንክ ስሊፕ በማምጣት ኩዩ ወረዳ ገቢዎች ቢሮ በማወራረድ ሰነዱን ከኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋ የያዘ ዝርዝር የዋጋ ሰነድ በፖስታ በማሸግ ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን እስከ 8:00 ሰዓት ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15000/ አስራ አምስት ሺህ / ብር ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለበት።
  5. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
  6. በሌላ ሰው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  7. ተጫራቾች ለሙያቸው ማረጋገጫ የስራ ልምድ እና የምስጋና ደብዳቤ ቢያቀርቡ ይመረጣል።
  8. መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0935 971 038 / 0911 775 600 በመደወል መጠየቅ ይቻላል

 

በሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender