በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል አላቂ የጽ/መሳሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽ/እቃዎች፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና እና የሞተር ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2018
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል አላቂ የጽ/መሳሪያዎች፣ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽ/እቃዎች፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና እና የሞተር ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም
-
ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው፣ የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱና በፌደራል ወይም በክልል ገንዘብ ጽ/ቤት በአቅራቢነት ሊስት የተመዘገቡበትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ዋናውን እና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
-
አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ሁሩታ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
-
ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በአቅራቢያችሁ የሚገኝ የታወቀ ባንክ በከፍያ ማዘዣ ወይም ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል።
-
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ ብር ብቻ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ የጽ/ቤቱ የግዥና ንብረት የስራ ጉዳይ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
-
በዋጋ አጻጻፍ ተራ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ የተደለዘው ዋጋ ተቀባይነት የለውም በተጨማሪም በእርሳስና ቀለም በሚጠጣ ብእር እንዲሁም ከተሰጠው ቦታ ውጪ የተፃፈ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
-
ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
-
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 15 የስራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታውም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15 የስራ ቀን 6 ሰአት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8 ሰአት ጽ/ቤቱ ለአመቺነቱ በመረጠው ቦታ ይከፍታል።
-
ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው የእቃ ዋጋዎች /የመወዳደሪያ ሀሳቦች/ የተጨማሪ እሴት ታክስ መካተቱንና አለማካተቱን መግለፅ ይኖርባቸዋል። ይህ ያልተገለጸ ከሆነ የተሰጠው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዳከተተ ይወሰዳል፡፡
-
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር
0223340092/93,0913395634, 0934951727,0920389358
በአርሲ ዞን የሎዴ ሄጦሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
