በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የጽህፈት መሣሪያዎች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የመኪና እና የሞተር ጎማና የተለያዩ መለዋወጫ ዕቃዎች
- የፈርኒቸር ዕቃዎች
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ እና የስፖርት ልብስ
- የግንባታ ዕቃዎች
- የተለያዩ ጀነሬተሮች
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል እና የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ የ2017 ዓ.ም መሆን አለበት፡፡
- በንግድ ሚኒስቴር በአቅራቢነት ዝርዘር የተመዘገበ፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ 30,000.00 /ሰላሣ ሺህ/ ብር በሲፒኦ /cpo/ ለእያንዳንዱ ዶክመንት ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንከ በተመሰከረ ሲፒኦ /cpo/ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ቀርቦ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነና ዕቃዎቹን በራሱ ሙሉ ወጪ በታዘዘ በ15 ቀን ውስጥ እስከ ጽ/ቤቱ ለማቅረብና ቆጥሮ ማስረከብ አለበት፡፡
- ተጫራቹ የዕቃውን ሞዴል ባልተገለጸበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ አብራርቶ መግለጽ አለበት፡፡
- ተጫራቹ የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልተው የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- በፈርኒቸር ዕቃዎች ላይ የምትወዳደሩ ድርጅቶች የፈርኒቸሮችን ዲዛይን ከዋጋው ጋር ማቅረብ እና ካሸነፈ ገጣጥሞ ማስረከብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቹ ለሚያቀርባቸው የደንብ ልብሶች:- የላፕቶፕ ቦርሳዎች ለመ/ቤቱ አስፈላጊ ለሆኑ ዕቃዎች ሳምፕል /ናሙና/ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቹ የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ5/13/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጠናቆ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከግዥ ክፍል 13 ቁጥር በመቅረብ የዕቃዎቹን ዝርዝር እና ለዚሁ የተዘጋጀውን የተጫራቾችን መመሪያ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ ሶስት መቶ /300.00/ ብር ከኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዢ ክፍል 13 ቁጥርበመግዛት የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው፡፡
- የሚወዳደሩበትን ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
- ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ፍቃድንና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን የሚገልጽ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ሲፒኦ /CPO/ ለየብቻ በ5 /አምስት/ ፖስታዎችን በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታው ሣጥን በግዥ ከፍል ቁጥር 13 ውስጥ ክፍት መሆኑን አውቃችሁ እስከ 16ኛው ቀን 4:00 ፖስታዎችን በፈለጋችሁት በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በኦርጅናል ፈንታ ኮፒ አድርገው የተለያዩ የዕቃ ዓይነቶች መወዳደር ይችላሉ፤ (ለምሣሌ computer: Lap Top HP, Note Book Lenevo) ቀለሞችን፣ ጎማዎችን፣ የጽዳት ዕቃዎችን የመሳሰሉትን በተለየዩ ገጽ ፎቶ ኮፒ በመሙላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- VAT 7.50 % እና TOT 2% ከሚገዛዉ ዕቃ የሚቆረጥ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የደንብ ልብስ ጨርቅ ናሙና ከፖስታው ጋር አሽጎ ማቅረብ አለበት።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0913357097 ወይንም 0917273702
በኢሉባቦር ዞን አልጌ ሣቺ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት
