በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 06 በምስራቅ በር ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚ በታች ለተዘረዘሩት ሎት1 አላቂ የቢሮ እቃ ፣ ሎት2 አላቂ የትምህርት እቃ፤ ሎት3 የደንብ ልብስ ፣ ሎት4 ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ሎት5 የፅዳት ዕቃ ፣ ሎት6 ቋሚ ዕቃ ፣ ሎት7 የህክምና ዕቃ ፣ ሎት8 የደንብ ልብስ ስፌት ፣ሎት 9 ህትመት፣ ሎት 10 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ፣ ሎት 11 የማሽነሪ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 06 በምስራቅ በር ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚ በታች ለተዘረዘሩት ሎት1 አላቂ የቢሮ እቃ ፣ ሎት2 አላቂ የትምህርት እቃ፤ ሎት3 የደንብ ልብስ ፣ ሎት4 ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ሎት5 የፅዳት ዕቃ ፣ ሎት6 ቋሚ ዕቃ ፣ ሎት7 የህክምና ዕቃ ፣ ሎት8 የደንብ ልብስ ስፌት ፣ሎት 9 ህትመት፣ ሎት 10 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ፣ ሎት 11 የማሽነሪ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ C.P.O ማቅረብ አለባቸው።
|
ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
ሎት 1 |
አላቂ የቢሮ እቃ |
46,000 |
|
ሎት 2 |
አላቂ የትምህርት እቃ |
14,000 |
|
ሎት 3 |
የደንብ ልብስ |
30,000 |
|
ሎት 4 |
ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ |
18,000 |
|
ሎት 5 |
የፅዳት እቃ |
28,000 |
|
ሎት 6 |
ቋሚ እቃ |
20,000 |
|
ሎት 7 |
የህክምና እቃ |
2,000 |
|
ሎት 8 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
15,000 |
|
ሎት 9 |
ህትመት |
4,000 |
|
ሎት 10 |
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች |
1,500 |
|
ሎት 11 |
የማሽነሪ ጥገና |
3,000 |
- የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 5 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በማግስቱ 4፡30 በት/ቤቱ ቤተ መጻሀፍት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንሰፖርት ም/በር ቁ.2/ ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በሚወዳደሩበት የሎት መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ድምር መጠን ልክ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አማራጭ ጨረታ አይፈቅድም ግዢ ፈፃሚው
- የታወቁ ጉዳቶች የካሳ ክፍያ ገንዘብ መጠን በቀን 0.1% ይሆናል
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- መገናኛ ቦሌ ክ/ከተማ ጀርባ በሚገኘው ምስራቅ በር ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ሲሆን ስልክ ቁጥር 0116676650.
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 06 በምስራቅ በር ቁ.2
