የወሊሶ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት ለሴክተር መ/ቤቶች የሰራተኛ የደንብ ልብሶች፣ የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች እና የሞተር ሳይክሎችን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ ቁጥር 157/2002 እና የግዥ መመሪያን በመከተል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 01/2018
የወሊሶ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት አመት ለሴክተር መ/ቤቶች የሰራተኛ የደንብ ልብሶች፣ የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች እና የሞተር ሳይክሎችን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ ቁጥር 157/2002 እና የግዥ መመሪያን በመከተል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ዝርዝር ሁኔታዎች፡-
ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ ይሆናል፡፡ ስለዕቃዎቹ ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር) ብቻ በሲንቄ ባንክ በወሊሶ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ሒሳብ ቁጥር 1071027311218 በማስገባት በወሊሶ ከተማ ገቢ ጽ/ቤት ደረሰኝ በመቁረጥ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር ይዘው በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት የወሊሶ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 26 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
የተጫራቾች ግዴታዎች፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያለቸው፤ እንዲሁም በፌዴራል ገ/ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃ እና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጠቅላላ ግዥ ህጋዊ ከሆነ ባንከ የተረጋገጠ CPO 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ የኢትዮጵያ ብር) ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቹ የማጭብርበር፣ የሙስና፣ የማታለልና የማስገደድ ድርጊት የማይፈጽም መሆኑን ለማረጋገጥ ግዴታ በመግባት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን ቅጽ ሞልቶ በመፈረም ማስገባት አለበት፡፡
- ማንኛውም አሸናፊ ድርጅት ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% ውል የገቡበትን የግዥ ሂደቱ እስኪያልቅ ድረስ አጠናቀው እስኪጨርሱ ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን በአየር ላይ የሚውልበት ቀን በመሆኑ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ያለ ስርዝ ድልዝ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ሁሉንም ማስረጃ እና ሰነድ በኦሪጅናል እና በኮፒ በመለየት በኤንቨሎፕ በማሸግ በወሊሶ ከተማ ገ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 26 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን የመክፈቻ ስነ-ስርዓት እያስተጓጉልም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀኑ በዓል ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-3-41-30-12 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወሊሶ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
