የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለመምሪያውና ለተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ አልባሳት፣ የፅህፈት ዕቃዎች፣ የህትመት እቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ መስተንግዶ፣ የግንባታ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመድሃኒትና የላብራቶሪ ሪኤጀንት፣ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር እቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የGenerator.lift እና Fire Pump ጥገና (Preventive Maintenance) የመኪና እጥበት እና ግሪስ እና የእስረኛ ቀለብ በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም በማስፈለጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

|
ሎት |
የሚገዙ እቃዎች የሎት ዝርዝር |
ሲፒኦ |
|
ሎት 1 |
የደንብ አልባሳት |
10,000 |
|
ሎት 2 |
የፅህፈት ዕቃዎች |
3,000 |
|
ሎት 3 |
የህትመት ዕቃዎች |
3,000 |
|
ሎት 4 |
የፅዳት ዕቃዎች |
2,000 |
|
ሎት 5 |
መስተንግዶ /ውሃ እና ቆሎ/ |
10,000 |
|
ሎት 6 |
የግንባታ ዕቃዎች |
3,000 |
|
ሎት 7 |
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች |
5,000 |
|
ሎት 8 |
የመድሃኒት እና የላብራቶሪ ዕቃዎች |
3,000 |
|
ሎት 9 |
የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር ዕቃዎች |
4,000 |
|
ሎት 10 |
የመኪና ጎማ |
10,000 |
|
ሎት 11 |
የGeneretor.Lift እና Fire Pump ጥገና (Preventive Maintenance) |
5,000 |
|
ሎት 12 |
የመኪና እጥበት እና ግሪስ |
4,000 |
|
ሎት 13 |
የእስረኛ ቀለብ |
10,000 |
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የመንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ላይ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስም በተዘጋጀው በባንክ በተመሰከረለት የባንክ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ለ60 ቀናት ነው።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ሾላ ገበያ በሚገኘው በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እንዲሁም በ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን በመቱ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ከስራ ቀናት ውጪና የክብረ በዓል ቀናት ከዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ካላንደር ወይም ስራ የማይኖርበት ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-6-63-90-02/ 011-6-67-64-82
የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ