Tender Detail

Tender Details


የነቀምቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም ትምህርትና ሥልጠና ዘመን ለሥልጠና ግብዓት የሚውሉ የኮንስትራከሽን፣ የፈርንኒቸር ዕቃዎች፣ የማሽን፣ የኤሌከትሮኒክስ፣ የኤሌክትሪካል፣ የአውቶ፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ኮምፕዩተርና የኮምፑዩተር ዕቃዎች እና የመኪና ጎማ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የነቀምቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 . ትምህርትና ሥልጠና ዘመን ለሥልጠና ግብዓት የሚውሉ የኮንስትራከሽን፣ የፈርንኒቸር ዕቃዎች፣ የማሽን፣ የኤሌክትሮኒስ፣ የኤሌትሪካል፣ የአውቶ፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ ኮምፕዩተርና የኮምፑዩተር ዕቃዎች እና የመኪና ጎማ ለመግዛት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፡-

  1. በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የዘመኑ የገቢ ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የተጨማሪ እሴት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NUMBER) ያላቸው
  4. የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. ማንኛውም ተጫራች ከመንግስት ግዥ ያልታገደ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ አለበት፣
  6. አቅራቢዎች ተጫርተው ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት እስከ ነቀምት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት፤
  8. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ መተው ወይም ሌላ ሀሳብ ማቅረብ በፍፁም አይችሉም፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፤
  10. ጨረታውን ለማደናቀፍ የሞከረ ማንኛውም ተጫራች መንግስት ከሚያወጣው ጨረታ ውጭ ይሆናል፤
  11. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ከፍሎ፣ ነቀምቴ ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በሚገኘው ክፍል መውሰድ ይችላል
  12. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች አሸና መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 10 ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል መቀበል አለበት፡፡
  14. ከዚህ በፊት ማለትም ኮሌጃችን ባወጣው ጨረታ 2017 . በግልጽ ጨረታውን ካሸነፉ ዋጋ ስለጨመረ ዕቃዎቹን አናቀርብም በሚል ምከንያት ሲፈጥሩ የነበሩ ተጫራቶች በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችሉም፡፡
  15. ተጫራ ዕቃዎቹን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን specification" ሳይለውጡ የጨረታውን መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ዋጋውን ከነ ተጨማሪ እሴት ታክስ በመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  16. የተጠየቀው "specification" በባዶ ቦታ ላይ በትክክ ሞልተው ያላቀረቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም
  17. ተጫራቾች የዘዙት ሰነድ ዋጋውን ከሞሉ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተደረጎበት ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በሁለት ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው
  18. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ለተጫራቾች ፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን 16ኛው ቀን 400 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ከታሸገ በዛው ዕለት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 415 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ቀኑ አመት በዓል ቅዳሜ ወይም እሑድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  19. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  20. ሰነዱ ገቢ የሚደረግበትና የሚከፈትበት ቦታ ነቀምቴ ፖሊ ኒክ ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ክፍል ይሆናል፡፡

ድራሻ

ነቀምቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች

0986074636 /0576612454 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

 

በኦሮሚያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ሙያ ቢሮ የነቀምቴ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

 

Save Tender