በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዥ ለመፈፀም ስለምፈልግ በዚህም መሰረት ፡- ሎት1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ ዕቃ ሎት2 አላቂ የፅዳት እቃዎች ሎት3.የደንብ ልብስና የስፖርት እቃዎች እና ትጥቅ ሎት4.የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ቋሚ እቃዎች ሎት5.የትምህርት መማሪያ እቃዎች እና የላብራቶሪ እቃ ሎት6. የህትመት ስራ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግዥ ለመፈፀም ስለምፈልግ በዚህም መሰረት ፡- ሎት1. አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ ዕቃ ሎት2 አላቂ የፅዳት እቃዎች ሎት3.የደንብ ልብስና የስፖርት እቃዎች እና ትጥቅ ሎት4.የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ቋሚ እቃዎች ሎት5.የትምህርት መማሪያ እቃዎች እና የላብራቶሪ እቃ ሎት6. የህትመት ስራ
-
በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው በመስኩ ህጋዊ ሰነድ እና ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ፣የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
ተጫራቾች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሆኑና ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ሙሉ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን እና አድራሻውን መፃፍ አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 250.00(ሁለት መቶ ሀምሳ ብር) በመከፈል በአራዳ ክ/ከተማ ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 5 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጠኛ ቀን ከጠዋት4፡00 ሠዓት ታሽጎ ጠዋት4፡30 ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 የሚከፈት ይሆናል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸውን ሎት 1,2,3, 5,6 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 4 በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጭና ከቫትጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ መስከበሪያ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
-
የጨረታ አሸናፊ ከተቋሙ ጋር ውል ለመዋዋል በቅድሚያ የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
-
አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይምበክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- ፒያሳ ከመብራት ሀይል ወደ እሪበከንቱ በሚወስደው መንገድ ጎጀብ ጥርስ ህከምና ጎን
ለበለጠ ማብራሪያና ጥያቄ ስልክ ቁጥር 01112664-18/09-12-85-03-39/09-11-38-31-11
በአራዳ ክ/ከተማ ህብረት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
