የአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት በጨረታ ቁጥር አየ/አ/2ኛ/ደረጃ ት/ቤት 01/2018 መሰረት የ2018 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማር የሚውሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
የአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት በጨረታ ቁጥር አየ/አ/2ኛ/ደረጃ ት/ቤት 01/2018 መሰረት የ2018 በጀት ዓመት ለመማር ማስተማር የሚውሉ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የእቃው አገልግሎት አይነት |
የግዥ ሎት ምድብ |
የግዥው ምድብ |
የጨረታው ማስከበሪያ የብር መጠን |
|
1 |
የአላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች |
ሎት 1 |
እቃ |
5000 |
|
2 |
የደንብ ልብስ |
ሎት 2 |
እቃ |
5000 |
|
3 |
የፅዳት እቃዎች |
ሎት 3 |
እቃ |
5000 |
|
4 |
የፈርኒቸር እቃዎች |
ሎት 4 |
እቃ |
5000 |
|
5 |
የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ እቃዎች |
ሎት 5 |
እቃ |
5000 |
|
6 |
የህንፃ መሳሪያ እቃዎች |
ሎት 6 |
እቃ |
5000 |
|
7 |
የስፖርት እቃዎች |
ሎት 7 |
እቃ |
5000 |
|
8 |
ህትመት |
ሎት 8 |
አገልግሎት |
3000 |
|
9 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
ሎት 9 |
አገልግሎት |
3000 |
|
10 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና |
ሎት 10 |
አገልግሎት |
3000 |
|
11 |
መጽሀፎችና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች |
ሎት 11 |
እቃ |
3000 |
|
12 |
የፍሳሽ ማስወገጃ /ሽንት ቤት ማስመጠጥ/ |
ሎት 12 |
አገልግሎት |
2000 |
|
13 |
የውሃ መስመሮች ጥገና |
ሎት 13 |
አገልግሎት |
2000 |
|
14 |
የፈርኒቸር እቃዎች ጥገና |
ሎት 14 |
አገልግሎት |
3000 |
|
15 |
የትራንስፖርት አገልግሎት |
ሎት 15 |
አገልግሎት |
3000 |
|
16 |
ኬሚካሎች እና የላብራቶሪ የትምህርት መሳሪያዎች |
ሎት 16 |
እቃ |
5000 |
- ከሎት ቁጥር 8-15 የተጠቀሱት የአገልግሎት ግዢዎች በበጀት ዓመቱ አገልግሎቱ በሚፈለግበት ወቅት በሚታዘዘው መጠን ልክ ሲሆን ውሉ ጸንቶ የሚቆየው እስከ በጀት አመቱ መዝጊያ መሆኑ እናሳውቃለን።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤ የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና በ2018 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው፡፡
- ከአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ጥፋቶች ያልተሰረዙ ወይም የቅጣት ጊዜያቸው ያልተጠናቀቀ በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት እቃ ከላይ በየሎቱ በተቀመጠው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ CPO ሲዘጋጅ በአየር አምባ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስም መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ማንኛወም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለማስገባት በሚመጣበት ጊዜ ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች አብሮ ማስገባት አለበት ሳምፕል ለማቅረብ ምቹ ያልሆኑ እቃዎች በፎቶ ማቅረብ ግዴታ ሲሆን ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማናወዳድር መሆኑን በቅድሚያ ት/ቤት ይገልጻል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እንዲሁም CPO ከኮፒው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ እና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በማግስቱ ማለትም በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ቫተን ያካተተ ሆኑ መገለጽ አለበት፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ /10%/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ት/ቤት አሸናፊው ተጫራች ያቀረበው ዋጋ ሳይቀየር 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይቻላል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ ይኖርበታል፡፡
- ት/ቤቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ለሎት 15 የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ 2% ተመዘጋቢ የሆነ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል፡፡
አድራሻ፡- በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር ቦሌ ሚካኤል ሩዋንዳ ኤምባሲ ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ለበለጠ መረጃ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት
በስልክ ቁጥር፡- 011-8220132/011-8220137 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአየር አምባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት
