በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለሠራተኛ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመገልገያ ዕቃዎችና ለምርት አገልግሎት የሚውሉ የምርት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨ.ሰ.ቁ፡-NCB-AAMMI-001/2018
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለሠራተኛ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመገልገያ ዕቃዎችና ለምርት አገልግሎት የሚውሉ የምርት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት-1 የስቴሽነሪ ዕቃዎች
ሎት-2 የጽዳት ዕቃዎች
ሎት-3 የአደጋ መከላከያ እና የሥራ አልባሳት
ሎት-4 የምርት ቀለምና ኬሚካል ፈሳሾች
ሎት-5 የትራክተር ራዲያተር ኮር
ሎት-6 የምርት ግብዓት ጥሬ እቃ
ሎት-7 የትራክተር እና የፓምፕ መለዋወጫ
ሎት-8 የትራክተር ጎማዎች
- በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ያህል ሰነዱን አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት መውሰድ (መግዛት) ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት እታ ጋር ተዛማጅ የሆነ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፊቃድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግብር ክሊራንስ /ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ/የሚያስችል ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተጫራቹ ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡
- (ሀ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣
- (ለ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ የባንክ ጋራንቲው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት ሰነዱን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው አስተሻሸግ መሰረት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት አየርላይ የሚውል ሆኖ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 830 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም።
- ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 022110689/0912264680 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- አዳማ ከወንጂ ማዞሪያ ተቃራኒ አቅጣጫ 500ሜ ላይ
ስልክ ቁጥር:- 0221110689/0912264680 ፋክስ :- 0221111866 አዳማ
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
