በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት አማካኝነት በ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት የሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች ደንብ ልብስ የስፖርት ባለሙያዎች ደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማዎች የመኪና እስፔር ፖርቶች እቃዎች/፤ የሞተር ዘይቶች እና ሲሚንቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት አማካኝነት በ2018 በጀት አመት በመደበኛ በጀት የሁሉም ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ የቋሚ አላቂ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የስፖርት ባለሙያዎች ደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማዎች የመኪና እስፔር ፖርቶች እቃዎች/፤ የሞተር ዘይቶች እና ሲሚንቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው።
- ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት ነገርግን የኮምፒዩተር እና ተዛማጅ እቃዎች አቅራቢ የብር መጠኑ ከ200,000 በታች ቢሆንም የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡
- ለመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችል ።
- ተጫራቾች ጨረታው ላይ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና ሌላም መረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በሁለት ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው ማቅረብ አለባቸው።
- የሁሉንም እቃዎች ዝርዝር እስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ ካስቀመጠው ውጭ በራሱ ጊዜ እስፒስፊኬሽን የመጨመርና የመቀነሰ ወይም ያስቀመጠ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በዝ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እና በ16ኛው ቀን 2፡30-6:30 በተዘጋጀው ሳጥን በማስገባት በዚያው ቀን 8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በዝ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /በሰ.ፒ.ኦ/ ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ከሚወዳደሩበት ሰነዱ ላይ ከእንዱ ዋጋው እና ጠቅላላ ዋጋው ላይ ስርዝ ድልዝ ያደረገ ከጨረታው ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ የአንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ የሚለውን በጥንቃቄ ለያይተው መሙላት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆኑ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ትእዛዝ /ሰ.ፒ.ኦ/ በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው ዙሪያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የደንብ ልብስ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች ተቋሙ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት መሆኑ መታወቅ አለበት።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግስት ስራ ዝግ ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀንና ሰዓት በተመሳሳይ ጊዜ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከኦርጅናል ሰነዱ ላይ የንግድ ፍቃዱን ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ የማያስገባ ወይም ኮፒ አድርጎ ፖስታው ላይ ሳያስገባ ውጭ ላይ የተወ ከውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን ይታወቅ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው አካል ውል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ቀጥታ በአስቸኳይ በውሉ መሰረት ንብረቱን ዝ/ወ/በሚገኘው ሴ/መ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት
- ይህ ውድድር ለ 1/አንድ/ አመት ሙሉ ስለሆነ ከላይ የተዘረዘሩት እቃዎች በአመቱ ውስጥ ሲያስፈልግ የሚያቀርብ መሆኑን ይታወቅ ።
- ለበለጠ መረጃ 0334620050/53/49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል። ጽ/ቤቱ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዝቋላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት
