መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 117
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቁጥር አራት (4) ቅጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱትን ቁሳቁሶች ማለትም፡
- 140 የተለያዩ ሞዴል ያላቸው ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች፣
- ከአሉሚኒየም የተሰሩ በሮች፣ የአሉሚኒየም ዘንጎች፣ ቶቦላሬዎች፤ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ሼልፎች ፋይል ካቢኔቶች፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ዩፒኤስ፣ የውሃ ማጣሪያ፣ ፍሪጅ ፤ ቴሌቪዥን (ቶነር) የመኪና መለዋወጫዎችና የመኪና ባትሪዎች፣
- በሸራና በብረት የተሠሩ ወንበሮች፣
- የተነቃቀሉ ጣውላዎች፣
- የሽንት ቤት ሣህኖች፣
- የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎች፣
የጨረታ ሰነዱ በቁጥር 4 ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 160,000 (አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ብር ብቻ) ከያዘ ሲፒኦ ጋር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0930-79-64-13 ወይንም 0975-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
