በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኘው የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የአገልግሎት አይነቶች |
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
ህትመት ስራዎች |
1 |
5,000.00 |
|
2 |
ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
2 |
50,000.00 |
|
3 |
የፅዳት እቃዎች |
3 |
5,000.00 |
|
4 |
የተለያዩ አላቂ የቢሮ እቃዎች (የጽህፈት መሣሪያዎች) |
4 |
5,000.00 |
|
5 |
የደንብ ልብስ |
5 |
15,000.00 |
|
6 |
ቋሚ ፈርኒቸር ዕቃዎች |
6 |
15,000.00 |
|
7 |
የጥገና እቃዎች |
7 |
15,000.00 |
|
8 |
የሰው መድሃኒት |
8 |
50,000.00 |
|
9 |
የህክምና ዕቃዎች |
9 |
50,000.00 |
|
10 |
የመኪና ጥገና ወይም የጋራዥ አገልግሎት |
10 |
5,000.00 |
ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ ምዝገባ ያላቸው፤ የዘመኑ ግብር ለመክፈላቸው ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- አነስተኛ ጥቃቅን ተቋማት በአዋጁ መሠረት የተቋቋሙ አምራች በሆኑበት ዘርፍ ብቻ ወይም በሚያመርቱት እቃ ብቻ ካደራጃቸው አካል በሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተቋማቱ አምራች ባልሆኑበት ዘርፍ በዋስትና ደብዳቤ አናስተናግድም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁ. 7 መውሰድ ይቻላል።
- ከላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ በአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ስም በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱትን ሰነድ የምትወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመሙላት በየሎቱ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በሁለት ፖስታ አሽገው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሁሉም ዕቃ ናሙና /ሳምፕል/ማንዋል/ፎቶግራፍ/ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት በ11ኛ ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አለም ባንከ ጤና ጣቢያ በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለጨረታ የቀረበ ሳምፕል ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባለ በሁለት ወር ውስጥ ሳምፕሉን ካልወሰዱ ለተቋሙ ገቢ ይደረጋል፡፡
- በሎት 2 እና 6 ሳምፕል በካታሎግ ወይም በፎቶ ግራፍ አጉልቶ በሚያሳይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ካላቀረቡ መወዳደር አይችሉም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ናሙና ሲያመጡ በካርቶን ወይም በማዳበሪያ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በፌስታል የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የወሰዱት የጨረታ መመሪያ ሰነድ በየገፁ ፈርመው ክብ ማህተም በማድረግ ከኦሪጅናል ሰነድ ጋር በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ ልዩ ቦታ ትሮፒካል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጀርባ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-8-32-59-69 መደወል ይቻላል፡፡
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍል ከተማ የአለም ባንክ ጤና ጣቢያ
