Tender Detail

Tender Details


የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል በተለያዩ ሎት የተከፋፈሉ  የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የውሃ እቃዎች፣ የህንጻ መሳሪያዎች፣ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የመኪና የሞተር ዘይትና የተለያዩ የሞተር ቅባቶች፣ የእንስሳት የህክምና ቁሳቁስ እቃዎች በሳንፕሉ መሰረት የሚቀርብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዘብ /ቤት 2018 . በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል በተለያዩ ሎት የተከፋፈሉ  የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የውሃ እቃዎች፣ የህንጻ መሳሪያዎች፣ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ የመኪና የሞተር ዘይትና የተለያዩ የሞተር ቅባቶች፣ የእንስሳት የህክምና ቁሳቁስ እቃዎች በሳንፕሉ መሰረት የሚቀርብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች በኦርጅናልና በኮፒ ከመጫረታቸው ከሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. የሚገዛውን እቃና ዓይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለአንድ ሎት በመክፈል ኩታበር ወረዳ ገንዘብ /ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይቻላል።
  5.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ለሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ በእያንዳንዱ ሎት ዋጋ 40,000 /አርባ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. /ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ድምር ነው፤
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኩታበር ወረዳ ገንዘብ /ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 415 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ነው።
  9. 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ጨረታው 430 ላይ ይከፈታል።
  10. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ለተጨማሪ ማብራሪያ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0334488011/033448228 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

በደቡብ ወሎ ዞን የኩታበር ወረዳ ገንዘብ /ቤት

 

Save Tender