Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2018 በጀት አመት በ13 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ሴ/ህ/ማ/ጉ/ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2018 በጀት አመት በ13 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት ቁጥር

የሚገዛው እቃ/አገልግሎት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

ሎት1

የተለያዩ የፅዳት እቃዎች ግዥ

50,000.00 CPO

 

ሎት2

ደንብ ልብስ እና የህፃናት አልባሳትና ጫማዎች ግዥ

100,000.00 CPO

 

ሎት3

የተለያዩ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች ግዥ

100,000.00 CPO

 

ሎት4

የተለያዩ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች ግዥ

50,000.00 CPO

ሎት5

የህፃናት ፍራሽ እና ብርድ ልብስ ግዥ

50,000.00 CPO

ሎት6

የተለያዩ የሴት ፀጉር ቤት እቃዎች ግዥ

50,000.00 CPO

ሎት7

የተለያዩ የአካል ድጋፍ እቃዎች ግዥ

100,000.00 CPO

ሎት8

ዶሮ፤የዶሮ ቤት/ኬጂ/፤ በግ፤የዶሮና የበግ መኖ ግዥ

100,000.00 CPO

ሎት9

የልብስ ስፌትና የቆዳ መስፊያ ማሽን ግዥ

100,000.00 CPO

ሎት10

የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች

50,000.00 CPO

ሎት11

የተለያዩ የህፃናት መጫወቻ እቃዎች እና ምንጣፎች

50,000.00 CPO

ሎት11

የተሽከርካሪ ጎማና ምንጣፍ/ታፒሴሪ/ ሥራ ግዥ

50,000.00 CPO

ሎት13

የኮምፒውተር ጥገና

50,000.00 CPO

 

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና የፋይናንስ መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /IN/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ NAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በአካውንት ቁጥር 1000009650559 በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ከቢሮው ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

 

6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔስፊኬሽኑ መሰረት ብቻ ሞልተው እና አሽገው በአንድ ኤንቨሎፕ ላይ ኦርጂናልና ኮፒ ብለው በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

8. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

9. ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡

10. የጨረታ ማስከበሪያ በCPO ነው

ማሳሰቢያ:-

የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።

አድራሻ፦ አ/አ/ሴ /ህ/ማ/ጉ/ ቢሮ ደጃች ውቤ ከጊዮርጊስ ቤተከርስቲያ ወደ አፍንጮ በርበሚወስደው መንገድ የስድስት ኪሎ/ፈረንሳይ ታክሲ መጫኛ ጋር ህንጻ 1888 ላይ 2ኛ ፎቅ

ስ.ቁጥር 0942129792/0947951760

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ

Save Tender