Tender Detail

Tender Details


የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በተለያየ መንገድ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ምግብ ነክ ዕቃዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር -14/2018

 

የሐዋሳ ጉምሩክ //ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በተለያየ መንገድ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 ንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ሳይ አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ምግብ ነክ ዕቃዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ሲሆን ከፍተኛ የመሸጫ ዋጋው ከብር 500 መቶ ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም፣፣
  2. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታዉን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያዉ ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 200 እስከ 600 ከሰዓት 700 እስከ 11:00 ሰዓት፣ ቅዳሜ 200 እስከ-600 ሰዓት ድረስ በቅ//ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት በተጫራቹ ስም መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ //ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክ ደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል።
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ //ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ ለሀራጅ ጨረታ ለሁለት ኮድ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) እና 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ለአንድ ኮድ የአልባሳትና ጨርቃጨርቅ ዕቃዎች ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) (C.P.O) ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 6ኛው (በስድስተኛው) ቀን ጠዋት 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 405 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ///ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ሂደቱ ካለቀ 10 ደቂቃ የሀራጅ ጨረታው የሚጀምር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጨረታው በበዓል እሁድ ቀን የሚዉል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥለዉ የስራ ቀናት ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበዉ ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበዉ ዋጋ በሚለዉ ርዕስ ስር በተሰጠዉ ፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ንቬሎፕ ወይም ፖስታ መቅረብ አለባቸው ከዚህ ሰነድ ውጭበሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ // ቤቱ ለመቀበል አይገደድም፡፡
  6. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው ስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡ በተጨማሪ ማንኛዉም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ //ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳዉቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
  9. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ//ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውምበተጨማሪ /ቤቱ የማይነበብ የሰነድ ኮፒ የመቀበል ግዴታ የለበትም፡፡
  11. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸዉን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5(አምስት) የስራ ቀናት ስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ//ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል፡፡
  13. //ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ው።

 

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-53-96/ 046-212-65-95

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ //ቤት

 

Save Tender